1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዛሬ በይፍ ተጀመረ

ማክሰኞ፣ ጥር 12 2012

የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዛሬ በይፍ ተጀመረ። ስዊዘርላን ዳቮስ ዛሬ የጀመረዉና ለአራት ቀናት የሚዘልቀዉ የዘንድሮዉ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዋና ንግግር አቅራቢ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሆናቸዉ ተመልክቶአል። የመካከለኛዉና የሊቢያ ግጭት የዓለም ከባቢ አየር ሙቀት መጨመር የመነጋገርያ ርዕሶች ናቸዉ ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3WbH2
Schweiz Weltwirtschaftsforum 2020 in Davos
ምስል Reuters/D. Balibouse

የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዛሬ በይፍ ተጀመረ። ጉባዔዉን በንግግር የከፈቱት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸዉ። የፕሬዚዳንት ትራምፕ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በአብዛኛዉ የገዛ ራሳቸዉን የፖለቲካ አመራር በማወደስ የተሞላ መሆኑ ተዘግቦአል። በሌላ በኩል ትራምፕ ታዋቂዋ የከባቢ አየር ንብረት ተቆርቋሪና ተሟጋች ስዊድናዊት ግሬታ ቱዎንበርግን አንስተዉ መፎተታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። የዳቮሱ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ በይፋ ከመጀመሩ ቀደም ሲል፤ የዓለም ፖለቲካ እና ኤኮኖሚ የዓለም አየር ንብረት ሙቀትን መታደግ አልቻሉም ስትል ስዊድን ወቀሳዋን አሰምታ ነበር። ስዊዘርላን ዳቮስ ዛሬ የጀመረዉና ለአራት ቀናት የሚዘልቀዉ የዘንድሮዉ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዋና ንግግር አቅራቢ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሆናቸዉ ተመልክቶአል። ትራምፕ በሚቀርቡበት መድረክ በተለይ የዓለም የከባቢ አየር ለዉጥን መታደግ፤ በመካከለኛዉ ምስራቅ እና የሊቢያ ዉጥረት መፍታት የሚሉ ርዕሶች ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።    

 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ