«የደድ ባድ» የፍቅር ሃገር
እሑድ፣ የካቲት 11 2010ማስታወቂያ
የተለያዩ ቋንቋዎችን በመጠቀም በሚያነሳቸው ሃሳቦች ታዳሚውን የመያዝ አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ በመድረክ ላይ ያዩት ይመሰክራሉ። ሸምሱ የመድረክ ስራዎቹም በአዳራሹ የሚገኙ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ዩኒቨርስቲ እያለ በስልጤ ቋንቋ የቀልብ ገርባሻት የተባለ መጽሐፍ አሁን ደግሞ ሪያድ ከመጣ በኋላ የድድ ባድ የተሰኘ መድብል አሳትሟል። ብዙ ጊዜ መድረክ ላይ ሽልማት ይጎርፍለታል። ቀልዶቹ ዝም ብለው ቧልት አይነት አይደሉም ማህበራዊ ህጸጾችን እያወጡ የሚተቹ ናቸው። በዚህ ዝግጅታችን ሸምሱን ሪያድ ላይ በስልክ አግኝተን ስራዉን የሥነ-ፅሑፍና የመድረክ ልምዱን እንዲያጫዉተን ጠይቀነዋል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።
አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ