1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃው የሳይንስ አካደሚ፣

ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 2004

በተለያዩ አገሮች፤ በተለይም በምዕራቡ ዓለም ባሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ አያሌ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ፣ በማስተማርና በምርምር ተግባር ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ የታወቀ ነው።

https://p.dw.com/p/RrpH
ምስል DW

ይህ ከትውልድ ሀገር እይታ አኳያ ፤ የምሁራን እጥረት፤ የዕውቀት ብክነት ሊባል ይችል ይሆናል። ይበልጥ ደግሞ ኢትዮጵያ ን ለመሰለ አዳጊ ሀገር፤ እንደፈረንጆቹ አባባል Brain Drain የሚሰኘው ለሌሎች Brain Gain ነው ማለት ይቻላል።

በትውልድ አገራቸው በኢትዮጵያ፤ በአካል ተገኝተው፣ በሥነ ቴክኒክ የፈጠራ ሥራ ዘርፍ፤ ዕውቀታቸውን ማካፈል ባይችሉም በዘመናዊው የመገናኛ ዘዴ፤ በኢንተርኔት ድረ-ገጽ ካገር ውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ምሁራን፣ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የመገናኛ መረብ የዘረጉት በአንግሊዝ ሀገርና በዴንማርክ በመዘዋወር ፤ አሁን ግን በፕሪቶሪያው የእስዋኔ የሥነ ቴክኒክ ዩኒቨርስቲ፤ በፕሮፌሰርነት የሚያገለግሉት የዚህ ሳይንስና ኅብረተሰብ ፕሮግራም ተባባሪአችን ዶ/ር ማሞ ሙጬ ፣ በቅርቡ የደቡብ አፍሪቃ ሳይንስ አካዳሚ አባል እንዲሆኑ ተመርጠዋል። ደስ የሚያሰኝ ሰናይ ዜና ነው። በአፍሪቃ ላቅ ያለ ግሥጋሴ ያደረገችው ሀገር የሳይንስ አካዳሚ አባል ሆነው ለመመረጥ የበቁት በምን መለኪያው እንደሆነ፤ ዶ/ር ማሞን አነጋግረናቸዋል።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ