1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን የሰላም ሰነድ መፈረም

ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2008

በደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎቹ ወገኖች ባለፈው ነሀሴ፣2008 ዓም በተፈራረሙት የተኩስ አቁም ውል ላይ ለቁልፍ የፀጥታ ጉዳዮች በቁርጠኝነት መፍትሔ ለመሻት የገቡትን ቃል ለማሟላት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራረሙ። አሁን የጦር አበጋዝ መኮንኖች ወደ ተግባር ለሚገቡበት ሂደት በዝርዝር እየተመካከሩ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1GuS9
Äthiopien Südsudan IGAD Unterzeichnung Friedensabkommen
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

ከአምስት ሳምንታት በፊት በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱንና የሽግግር መንግስቱን ለመመስረት ተዘጋጅቶ በነበረዉ ሰነድ ከተቃዋሚዎች አንደኛዉ ተቀናቃኝ ለመፈረም በማቅማማታቸዉ በድርድር መቆየቱ ይታወቃል። ዋናዉ ጉዳይ በሥልጣን ላይ ያለዉን ጨምሮ የፖለቲካ መሪዎቹ ከአንድ ዓመት ተኩል ዉጣ ዉረድ በኋላ የተነደፈውን ስምምነት መፈረማቸዉ ይታወሳል። ነገር ግን በጦር አዉድማዉ ላይ የሚገኙ የጦር መኮንኖች እኛ እየደማን እየተሰዋን እኛን ያላካተተ የሰላም ድርድር በማለት በየጊዜዉ እሮሮ በማሰማታቸዉ እንዲካተቱ ተደርጓል።


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ