1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ስምምነት ትግበራ እና ኢጋድ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2008

የደቡብ ሱዳንን የርስ በርስ ግጭት ለመግታትና የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ የሽግግር መንግስት ለመመስረት በዋና ከተማዋ ጁባ ከከተሙ ሰነባበቱ።

https://p.dw.com/p/1HVle
Äthiopien Südsudan IGAD Unterzeichnung Friedensabkommen
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

[No title]

በምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግስታት ባለሥልጣን በምህጻሩ ኢጋድ አደራዳሪነት የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ የማድረግ ሂደት ቢጀመርም በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል ቅራኔዎች አልጠፉም። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪየር አገሪቱን በ28 ግዛቶች ለመከፋፈል መወሰናቸው ይጠቀሳል። የቀድሞ የትግል አጋሮች ለሁለት አመታት ደግሞ በባላንጣነት በዓይነ ቁራኛ ሲጠባበቁ የከረሙት የፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና ሪየክ ማቻር ኃይሎች የሽግግር መንግስት ለመመሥረት እና ከሶስት ወራት በኋላ ምርጫ ለማካሄድ ልዩነቶቻቸውን መፍታት ይጠበቅባቸዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት የመተግባር ሂደት እና የኢጋድን ኃላፊነት አስመልክቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ