1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን አዲስ ምክትል ፕሬዝደንት መሾሟ፣

ረቡዕ፣ ሐምሌ 20 2008

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። መግለጫዉ ግንኙነታቸዉን ማቋረጣቸዉን ያመለከተዉ የምክትል ፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸዉን የለቀቁት ሪየክ ማቸርን የደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ የራሳቸዉ ፓርቲ ሊያገኛቸዉ ባለመቻሉ በአዲስ ምክትል ፕሬዝደንት መተካታቸዉን አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/1JWks
Äthiopien PK Südsudanesischer Botschafter
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

አምባሳደር ጀምስ ፒቲያ ሞርጋን በሰጡት መግለጫም ግንኙነታቸዉን አቋርጠዋል ያሏቸዉ የምክትል ፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸዉን የለቀቁት ሪየክ ማቸርን የደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ የራሳቸዉ ፓርቲ ሊያገኛቸዉ ባለመቻሉ በአዲስ ምክትል ፕሬዝደንት እንደተካቸዉ አመልክተዋል። አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ አክለዉም ከረዥም ዓመታት ጦርነት እና ትግል በኋላ ራሷን የቻለች ሀገራቸዉ ዉስጥ ለገላጋይነት የሚገባ የዉጭ ኃይል መንግሥታቸዉ እንደማይቀበል አብራርተዋል። መግለጫዉን የተከታተለዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ