1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደርግ ባለስልጣናትና የዕርቁ ጥረት አንድምታ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2003

የአራት ሃይማኖቶች አባቶች ባለፈው ቅዳሜ በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት እንዲፈቱ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን በይፋ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/Qgo2
የደርግ ባለስልጣናት በፍርድ ቤትምስል AP

ላለፉት 20 ዓመታት የታሰሩት እነዚህ ባለስልጣናት የሚፈቱበት ሁኔታ ህጋዊ መሠረቱ በእርግጥ ግልጽ አይደለም። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ጥረቱ የሚደገፍ ነው ብለዉታል። የተባበሩት መንግስታት የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ችሎት አቃቤ ህግ ዶክተር ያዕቆብ ሃይለማርያም ህገመንግስቱ መሰረት ከተደረገ እነዚህ የደርግ ባለስልጣናት እንዲፈቱ የሚፈቅድ አሰራር የለም። ግን ዕድሜአቸውና የያለባቸው የጤና ሁኔታ ግምት ውስጥ ከገባ ሊፈቱ የሚችሉበት ዕድል አለ ይላሉ። የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦች ማህበር በበኩሉ ጥረቱን የማይቃወም መሆኑን ተናግሯል። ይህ የሃይማኖት አባቶች ጥረት በዕርቅ ወይስ በይቅርታ ላይ የተመሰረተ? ህገመንግስቱ የማይፈቅድ ከሆነ የሃይማኖት አባቶቹ ጥረት መጨረሻው ምን ይሆን?

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ