1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ካሌ እና ስደተኞቿ

ሰኞ፣ ጥር 28 2010

በካሌ ውጥረቱ ጋብ ያለ ቢመስልም የስደተኞች ደህንነት አስጊ መሆኑን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2sAJg
Frankreich Einwanderung in Calais
ምስል picture-alliance/dpa/MAXPPP/O. Arandel

በካሌ የደህንነት ስጋት


በፈረንሳይዋ የወደብ ከተማ ካሌ ባለፈው ሳምንት በስደተኞች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት መብረዱ ተነገረ። ይሁን እና አሁንም በስፍራው ውጥረቱ ጋብ ያለ ቢመስልም በካሌ የስደተኞች ደህንነት አስጊ መሆኑን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንቱ ከአፍጋኒስታን ስደተኞች ጋር በተቀሰቀሰ ግጭት 5 ያህል የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች  በጥይት ተመተው በጽኑ መቁሰላቸውን ከ20 በላይደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል። በስፍራው የነበሩ ስደተኞችን ያነጋገረችው የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ