1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬይን የፓርላማ ምርጫ ዉጤትና እንደምታዉ

ሰኞ፣ ጥቅምት 17 2007

የምስራቅ ዩክሬይን ቀዉስ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ዩክሬይን አዲስ ፓርላማን መርጣለች። መፍቀሬ አዉሮጳ ፓርቲዎችም አብላጫ ድምፅን አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/1DcrJ
Symbolbild Ukraine Wahl Poroschenko
ምስል picture-alliance/dpa

በዩክሬይኑ ለ450 የምክር ቤት መንበሮች ነበር ዕጩዎች የተወዳደሩ ሲሆን ሩስያ የጠቀለለቻት የክሪም ማለትም የክሪሚያግዛት እና በመፍቀሬ ሩስያ የተያዘዉ የምስራቅ ዩክሬይን ተወካዮች መቀመጫ ሳይያዙ እንደሚቆዩ ተመልክቶአል። በምስራቅ ዩክሬይን የሚገኙት መፍቀረ ሩስያ ተገንጣዮች በበኩላቸዉ ለጥቅምት 23 ምርጫ እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል። ተገንጣዩቹ የጠሩት ምርጫ ግን በአዉሮጳዉ ህብረት ተቀባይነትን አላገኘም። በዩክሬይን ምርጫ ዉጤት የአዉሮጳ መንግሥታት አመለካከት ምን ይመስላል? ምንም እንኳ በዩክሬዩን የፓርላማ ምርጫ ቢካሄድም የምስራቅ ዩክሬይን ዉዝግብ አሁንም አለመፈታቱ የታወቀ ነዉ። ይህ ምርጫ ለዉዝግቡ መፍትሄ ያመጣ ይሆን? ዩክሬይን ከሩስያ ጋር ግንኙነት ላቋርጥ ብትል ሁኔታዉ የከፋ እንደሚሆን የአብዛኞች አመለካከት ነዉ ። የምስራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩስያንን ትረዳለች የምትባለዉ ሩስያ ከዩክሬይኑ የፓርላማ ምርጫ በኋላ፤ የሁለቱ ሃገራት የኤኮነሚ ግንኙነትስ በምን አይነት ይቀጥል ይሆን? የብራስልሱን ወኪላችን በስልክ አነጋግረነዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ