1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 2005

ዛሬ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተወሰኑ ሐሳቦች ከሌሎች ጎላ ብለው እየተደመጡ ነው። ሁለቱ እጩዎች የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እና ተፎካካሪያቸው ሬፓብሊካዊው ሚት ሮምኒ ባለፉት የምርጫ ዘመቻ ሳምንታት በተለያዩ የሀገሪቱ ግዛቶች ከባድ ፍልሚያ አካሂደዋል። ቨርጂኒያም ከነዚሁ ግዛቶች መካከል አንዷ ነበረች።

https://p.dw.com/p/16dqI
People vote in the U.S. presidential election at a polling station set up for those affected by Hurricane Sandy, in an art gallery at John Jay College, in New York November 6, 2012. REUTERS/Chip East (UNITED STATES - Tags: POLITICS USA PRESIDENTIAL ELECTION ELECTIONS)
ምስል Reuters

«ከአራት ዓመታት በፊት ምርጫውን ያሸነፉት ዲሞክራቶች ነበሩ። አሁን ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ሪፐብሊካንን ለመምረጥ እየሄድን ነው።

የሂሳብ አያያዝ ባለሙያዋ የቬርጂኒያ ነዋሪ ክርስቲያን ማርስቶን ናቸው; በቬርጂኒያ ሚት ሮምኒ እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ ሆነው የሚናገሩት። በተለምዶ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን የሚሸጡበት  «ሚዶው ኢቨንት» በተባለ የመዝናኛ ቦታ ከባለቤታቸው ማን ክሪስ ጋር  የሪፐብላካኑን እጩ ፕሬዚዳንት  ሚት ሮምኒን በመጠበቅ ላይ ናቸው። በዛሬው እለት ብቻ ሮምኒ በቬርጂኒያ ሶስት የምርጫ ዘመቻ ንግግር ያደርጋሉ። ማርቶንና ባለቤታቸው  የሚኖሩት ከቨርዳም ዋና ከተማ ሪችመንድ ወደ ሰሜን በምትገኘው አንድ መንደር  ነው፣ የዚህ መንደር ነዋሪዎች መሬት አራሾችና ከብት አርቦዎች ናቸው። ክርስቲያል ማርስቶን ቀድሞውኑ ለሮምኒ ድምጽ ሰጥተዋል። እንደ እሳቸው አስተያየት አሁን የሚታየው የኢኮኖሚው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢው ችግር ነው፣

«ቤተሰቦቼና ጓደኞቻ አሁን ባሉበት ሁኔታ ሲቸገሩ ማየት በቅቶኛል። ይህች ሀገር እኔ የማውቃትና ያደግኩባት  አሜሪካ አይደለችም። »
 
ከበስተጀርባው የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራ፣ የአዝመራ ክምርና ትራክተር የሚታይበት ግዙፍ ስዒል የተሰቀለበት መድረክ ላይ ቆመው፣ ሚት ሮምኒ እንደ ወትሮው ባለ አምስት ነጥብ እቅዳቸውን እየደጋገሙ፣ አሜሪካን እንዴት መልሰው በሁለት እግሯ እንደሚያቆሟት ይናገራሉ። እዚህ ሥፍራ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎችን ማሳመኑ ሚት ሮምኒን እምበዛም አያስፈልጋቸውም፣

«የዚህ ምርጫ  ውጤት ብዙ  ነገሮችን አስከትሎ እንደሚመጣ ይገባችኋል ብዬ አምናለሁ። አሁን ባለንበት ሁኔታ እንቀጥል ብለው የሚያምኑ ብዙ እንዳሉ አውቃለሁ። ነገሮች በመልካም ሁኔታ እየሄዱ ናቸው ብለው ያምናሉ።  እንደነ እምነት አሁን ያለንበት ሁኔታ ለአሜሪካ ትክክለኛው መንገድ ብዬ አላምንም።  ዞሮ ዞሮ አሜሪካ ቃል የተገባላትን እውነተኛ ለውጥ  ትፈልጋለች። ይህን ለውጥ ለአሜሪካ ህዝብ እናመጣለን። »

ኦባማና ሮምኒ በምርጫ ዘመቻ  የመጨረሻ ሰዓታታት በቬርጂኒያ አንገት ለአንገት እየተናነቁ ይገኛሉ። በኦህዮም እንዲሁ ትንቅንቁ ቀላል አይደለም። በፍሎሪዳ፣ ፔኒስላቪያ, ሚቺጋንንና ሚኔሶታም እንዲሁ። በነኚህ ስፍራዎች ነው ሁለቱ እጩ ተመራጮች ትኩረት ሰጥተው የተንቀሳቀሱበት። ሌሎች ቦታዎች ብዙም ትኩረት አላገኙም። ምክንያቱም በአሜሪካ ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ባጠቃላይ አብዛኛውን ድምጽ ማግኘት ብቻ የምርጫውን ውጤት አይወስነውም።

የእያንዳንዱ  ግዛት አስተዳደር  በእንግሊዘኛ «ኤሌክተር» የሚባሉ  መራጮችን ይልካሉ። እነኚ መራጮች ማን ፕሬዚዳንት መሆን እንዳለበት ይወስናሉ። 538 መራጮች ሲኖሩ 270 ድምጽ ያገኘ እጩ ተመራጭ አሸናፊ ይሆናል።  በብዙ ግዛቶች አሸናፊው ቀድሞውኑ ታውቆ የተቀመጠ ነው።  ለምሳሌ ካሊፎርኒያ ኦባማን ቴክሳስ ደግሞ ሮምኒን መርጠዋል።
በዋሽንግተን በስተደቡብ በትምገኝ በሪችሞንድ ፕሬዚዳንት ኦባማ ብዙ ደጋፊዎች አሏቸው።  ምክንያቱም ሃምሳ በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ ጥቁር አሜሪካውያን ናቸው። ከነሱም 25 በመቶ ከድህነት ወለል በታች ይኖራሉ።  ከሁለት ሳምንታት በፊት ኦባማ ወደ ከተማዋ በሄዱበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሰዓታት ቆመው ይጠብቋቸው ነበር።  የ19 ዓመቷ አንድሪያ አኩና ከነሱ አንዷ ናት፣

«ብዙ መልካም እቅዶች አሏቸው። ተንደላቀው በወርቃማ ማንኪያ እየተመገቡ አይደሉም ያደጉት። መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ለዛ ነው አሁን ፕሬዚዳንት መሆን የሚገባቸው»

ኦባማ የብዙ አሜሪካውያን ሴቶች ድጋፍ ቀንሶባቸዋል። ብዙ ነጭ መራጭ ወንዶችም ምርጫቸውን ሮምኒ አድርገዋል። አናሳ ቁጥር ያላቸው ህዝቦችና ጥቁር አሜሪካውያን ግን አሁንም ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ታማኝነት አልቀነሱም። ኦባማም ቢሆኑ የሪችሞንድ ነዋራዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ድጋፋቸውን እንዳይነፍጓቸው ሲጠይቂ በጋለ ስሜት ታጅበው ነበር፣

«ድምጻችሁን እፈልጋለሁ። እዚህ የመጣሁት አሜሪካን ወደ ፊት ትራመድ ዘንድ እርዳታችሁን ለመጠየቅ ነው።»

በቬርጂኒያ ለኦባማ ያለው ድጋፍ ከአራት ዓመት በፊት እንደ ነበረው አይደለም።  በዚያን ጊዜ በዚህ ስፍራ የዴሞክራቶች የምርጫ ዘመቻ ጽህፈት ቤት ትልቅ ነበር። ከአሁኑ በይበልጥ በቁጥር  ብዙ ሰዎች በፍላጎታቸው ቀንና ሌሊት ተግተው ይሰሩ ነበር።

The 10 registered voters in the small village of Dixville Notch, New Hampshire wait to cast the first election day ballots of the U.S. presidential election moments after midnight November 6, 2012. REUTERS/Herb Swanson (UNITED STATES - Tags: POLITICS USA PRESIDENTIAL ELECTION ELECTIONS)
ምስል Reuters
Kenyan family members of U.S. Democratic Presidential candidate Barack Obama, including his step-grandmother Sarah Obama, second left, celebrate after his victory in the U.S. election was announced, at the family's homestead in Kogelo village, Kenya, Wednesday, Nov. 5, 2008. The village is where U.S. Democratic Presidential candidate Barack Obama's step-grandmother lives. Barack Obama's Kenyan family erupted in cheers Wednesday, singing "We are going to the White House!" as Obama became the first African-American elected president in the United States. (AP Photo/Matt Dunham)
ምስል AP
A man carries his dog as he waits in line to turn in his ballot during the U.S. presidential election, at a polling station set up for those affected by Hurricane Sandy, in an art gallery at John Jay College, in New York, November 6, 2012. REUTERS/Chip East (UNITED STATES - Tags: POLITICS USA PRESIDENTIAL ELECTION ELECTIONS ANIMALS)
ምስል Reuters

ክሪስቲያነ ቤርግማን

ገመቹ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ