1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ መብት ዘገባ

ዓርብ፣ የካቲት 21 2006

በዘገባዉ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል።

https://p.dw.com/p/1BHdB
ምስል dapd

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በየዓመቱ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ባለፈዉ የጎርጎሮሳዉያን ዓመት ሁለት ሺሕ አሥራ-ሰወስት በዓለም ሥለነበረዉ የሠብአዊ መብት ይዞታ ያጠናቀረዉን ዘገባ ትናንት ይፋ አድርጓል። ዘገባዉ የኢትዮዮጵያና የኤርትራን ጨምሮ የሁለት መቶ ሐገራትን የሠብአዊ መብት ይዞታ የዳሰሰ ነዉ። በዘገባዉ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል። ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ዘገባዉን ይፋ ሲያደርጉ እንዳሉት ሠብአዊ መብት የሚከበረዉ በሕግ-አዉጪዎች ዉሳኔ ሳይሆን እስክንድር ነጋን በመሳሰሉ ቆራጦች ትግል ነዉ። የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ