1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናትድ ስቴትስና የኩባ ግንኙነት መሻሻል

ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2007

ሁለቱ ሃገራት እዚያው ፓናማ ሲቲ ውስጥ ትናንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ለማካሄድ በቅተዋል ።

https://p.dw.com/p/1F66H
Bildergalerie Kuba Bildkombo Barack Obama Raul Castro
ምስል picture-alliance/dpa/Michael Nelson/Alejandro Ernesto

በፓናማ መዲና ፓናማ ከተማ ፣ የደቡብና ሰሜን አሜሪያ ሃገራት 30 ያህል መሪዎች በሚገናኙበት ጉባዔ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኩባ ፕሬዚዳንቶች ባራክ ዖባማና ራውል ካስትሮ ዛሬ በራት ግብዣ ላይ አብረው በመታደም እ ጎ አ ከ 1959 ዓ ም አንስቶ ጸንቶ የቆየውን የቀዝቃዛ ጦርነት ዘመን መቃቃር ከአነአካቴው እንደሚያስወግዱ ተነገረ። ትናንት ማታ የሁለቱ ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፤ ጆን ኬሪና ብሩኖ ሮድሪጌዝ፣ ታሪካዊ በተሰኘ ስብሰባ ተገናኝተው መወያያታቸው ተነግሯል።ኩባan ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ታኅሳስ ፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነትን እንደገና ለማደስ መስማማታቸው የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓናማ ከተማ ውስጥ ጉባዔው ደምቆ ከሚካሄድባት አካባቢ ውጭ ስላለው የላቲን አሜሪካን ቅጥ ያጣ ድህነት ይገልጻል ስለተባለው አሳሳቢ ሁኔታ ፤ የዓለም አቀፉ እጓላ ማውታ መንደር (Childres’Village) ኀላፊ ኢሪስ ሱጋስት እንዲህ ብለዋል።

«ከጉባዔው ሕንጻ በስተጀርባ ዐቢይ ችግር መኖሩን አያስክድም። በዓለም ውስጥ ፤ ከማንኛውም አካባቢ በይበልጥ አድልዎ የሚፈጸምበት ቢኖር ላቲን አሜሪካ ነው። ከላቲን አሜሪካ አገሮች መካከል ደግሞ ባጠ በነጣውና በሀብታሙ መካከል ልዩነት ይበልጥ የጎላበት ፓናማ ናት።»

ዩናይትድ ስቴትስና ኩባ ለብዙ አሥርት ዓመታት በመካከላቸው ሰፍኖ የቆየውን የቀዝቃዛው ጦርነት መንፈስ ወደ ጎን በመተው ግንኙነታቸውን ደረጃ በደረጃ ለማሻሻል እየጣሩ ነው ። ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ትናንት ለ2ተኛ ጊዜ በስልክ ተነጋግረዋል ። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ና የኩባው ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮ በስልክ የተነጋገሩት ዛሬ ፓናማ ውስጥ በሚካሄደው የደቡብና ሰሜን አሜሪካ ሃገራት ጉባኤ ላይ ለመገኘት ትናንት ፓናማ ሲቲ እንደገቡ ነበር ። ከዚህ ሌላ ሁለቱ ሃገራት እዚያው ፓናማ ሲቲ ውስጥ ትናንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ለማካሄድ በቅተዋል ። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪና የኩባው አቻቸው ብሩኖ ሮድሪጌዝ ያካሄዱት ዝግ ስብሰባ ረዝማ ያለና ፍሪያማ ነበር ሲል የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታውቋል ። ።ዋሽንግተን ኩባን በአሸባሪነት ከፈረጀቻቸው ሃገራት ዝርዝር ውስጥ እንደምታወጣም አስታውቃለች ።የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ