1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባብዌ ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ምስረታ

ሰኞ፣ የካቲት 2 2001

ከዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ጋር የአንድነት መንግስት ለመመስረት የተስማሙት የተቃዋሚው የንቅናቄ ለዲሞክራሲ ለውጦች ፓርቲ የMDC መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ የፊታችንን ረቡዕ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለመሰየም ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ

https://p.dw.com/p/GqQx
ምስል AP

። የዛሬ ዓመት መጋቢት የተካሄደውን የዚምባብዌ የመጀሪያ ዙር ምርጫ ውጤትን ተከትሎ ለወራት ከዘለቀው ብጥብጥና ውዝግብ በኃላ ተቃዋሚው MDC ከሙጋቤ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ጋር ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ለመመስረት የተስማማው በደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማህበረብ SADEC ሸምጋይነት ነው ። እንደ ፖለቲካ ተንታኞች አስተያየት ከሆነ ሳዴክ ሁለቱን ወገኖች በማግባባቱ ሂደት በተለይ በMDC መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ ላይ ከፍተኛ ጫና አድርጓል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ MDC በስደት ዚምባብዌ የሚኖሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያምን ወደ ኢትዮጵያ መመሰል እንደሚፈልግ አስታውቋል ።