1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባቡዌ ምርጫና የፖለቲከኞቹ ዉዝግብ

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2005

በሁለት ሺሕ ስምንቱ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ግን አዲሱ ፖለቲከኛ አሮጌዉን መሪ አሸነፉ።ሰዉዬዉ ተንገዳገዱ ግን አልወደቁም።እንዳይወድቁ መጀመሪያ፥-በፀጥታ አስከባሪዎችና በቻንግራይ ደጋፊዎች መካካል በተደረገዉ ግጭት ከሁለት መቶ ባላይ ሰዉ መገደል፥ ቻንጋራይ ሳይቀሩ በመቶ የሚቆጠሩ መደብደብ፥ መቁሰል፥ መታሰር፥ ብዙ ሺሕ መሰደድ ግድ ነበረበት።

https://p.dw.com/p/19KBi
Supporters of Robert Mugabe's ZANU-PF party hold a coffin as they act out the fake funeral of opposition leader Morgan Tsvangirai while celebrating Mugabe's recent election victory in Mbare on August 4, 2013. Zimbabwean President Robert Mugabe was declared the winner of a controversial presidential election with 2,110,434 votes, giving him 61% of the total and his challenger Prime Minister Morgan Tsvangirai 34% amid allegations of blatant vote rigging. AFP PHOTO / ALEXANDER JOE (Photo credit should read ALEXANDER JOE/AFP/Getty Images)
የሙጋቤ ደጋፊዎችምስል Alexander Joe/AFP/Getty Images

ሰዉዬዉ ጠንከር፣፥ጠጠር የሚል ጠላታቸዉን ወዳጅ፥ቀረብ፥ጠጋ፥ አመን፥ ያደረገ ወዳጃቸዉን ጠላት ማድረጉን ሠልጥነዉበታል።ሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ።በወጣት፥ ጎልማሳነታቸዉ፥-በጆሽዋ ንኮሞ፥ በንዳባኒኒግ ሲቶሌ፥ በሊዎፖልድ ታካዊራ፥ በኤድጋር ቴኬሬ ላይ የተለመማዱ፥የተራቀቁበትን ሥልት በእስተርጅና ሞርጋን ቻንግራ ላይ ደገሙት።እንደጠላት አርቀዉ፥ አሳስረዉ፥ አስደብድበዉ አልሸነፍ ቢሏቸዉ እንደ ወዳጅ ተሻረኳቸዉ።ሾሟቸዉ። ዘንድሮ ለዉግዘት ወቀሳ በማይመች የምርጫ ሥልት እንደገና ዘረሯቸዉ።የዚምባዌ ምርጫ ዉጤት፥ የሙጋቤ ሥልት፥ የተቃዋሚዎቻቸዉ ማንነት ያፍታ ቅኝታችን ትኩረት ነዉ።አብራችሁን ቆዩ።

                    
በምርጫዉ ዋዜማ።ካለፈዉ ሮብ በፊት የተደረጉ ሁለት ምርጫዎችን የተከታተሉት በደቡባዊ አፍሪቃ የሮማ ካቶሊካዊት የጳጳሳት ጉባኤ አባል ኦስካር ቬርምተር «ሙጋቤ ላሁኗና ለወደፊቷ ዙምባቡዌ የባይበጁ ያለፈ ታሪክ አካል ናቸዉ።» ይላሉ
                
«ሙጋቤ ያለፈዉ ዘመን ሰዉ ናቸዉ።ወጣቶቹ በተለይ ተስፋና ሥራ አጥወጣቶች አዲስ ተስፋ የሚሰጣቸዉ ይፈልጋሉ።»

አዲሱን ተስፋ ሰጪዉ በአንፃራዊ መመዘኛ አዲሱ የፖለቲካ ማሕበር ነዉ።ንቅናቄ ለዲሞክራሲያዊ ለዉጥ።MDC በእንግሊዝኛ ምፃሩ።የፓርቲዉ እጩ ፕሬዝዳት፥ የሐገሪቱ የእካሁን ጠቅላይ ሚንስትር ሞርጋን ቻንግራይ ግን «ከወደፊቱ ይልቅ» ያለፈዉ በተለይ የሁለት ሺሕ ስምንቱ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ትዝታ ነበር የማረካቸዉ።
                 
«(ሙጋቤ) ሽንፈትን ይቀበላሉ ብዬ አምናለሁ? በሁለት ሺሕ ሥምንቱ ምርጫ አሸንፌ ነበር።ግን ሥልጣን አላስረከቡም።»

ከአዲሱ ፓርቲ መሪ ይልቅ፥ የሰማንያ ዘጠኝ ዓመቱ አዛዉንት፥ አንጋፋ ፖለቲከኛ፥ በቄስ ቬርምተር ቋንቋ «ያለፈዉ ዘመኑ ሰዉ» ያሁኑንና የወደፊቱን ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ።
                   
«አንድም ታሸንፋለሕ አለያም ትሸነፋለሕ።ከተሸነፍክ ላሸነፊዎቹ እጅ መስጠት አለብሕ።»

አሉ-ተባባሉና ሮብ ከምርጫዉ ገቡ።ዉጤት፥ የዚምባቡዌ ምርጫ ኮሚሽን ሐላፊ ዳኛ ሪታ ማካራዉ፥ ቅዳሜ።
            
«የዛኑ-ፒኤፉ ሙጋቤ ሮበርት ጋብርኤል፥ ሥለዚሕ የተመረጡ ፕሬዝዳት ናቸዉ።»

የሥልሳ አንድ ዓመቱ የሙጋቤ ተቃዋሚ፥ ተጣማሪም ሞርጋን ቻንጋራይ ለሰወስተኛ ጊዜ ተሸነፉ።የሰማንያ ዘጠኝ ዓመቱ አዛዉንት፥ ያለፈዉ ዘመን ሰዉ የመጪዉ ዘመን መሪም ሆኑ።ሙጋቤ ተንገዳግደዉ ይሆናል።ተሸነፈዉ ግን አያዉቁም።

የፖለቲካን አንድ ሁለት፥ የመብት ነፃነት ትግል ሀሁን የተማሩ፥ የጀመሩት ከጆሽዋ ንኮሞ እና ከጓደኞቻቸዉ ነዉ።በ1960 ንኮሞ የመሠረቱትን ብሔራዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲን (NDP) ተቀየጠ።ያኔ የሠላሳ ስድስት ዓመት ወጣት ነበር።ያ ጥቁሮች የሚበዙበት ፓርቲ ለብሪታንያዋ ደቡብ አፍሪቃ፥ ለደቡብ አፍሪቃዋ ሮዴሽያ የነጭ ዘረኞች መንግሥት ታላቅ ሥጋት ነበር።

NDP ለነጮቹ አገዛዝ የሚፈጥረዉን ሥጋት ከሐራሬ፥ ከፕሪቶንያም ገዢዎች ይልቅ ፈጥነዉ የተረዱት ግን የለንደን ፖለቲከኞች ነበሩ።የያኔዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሐሮልድ ሜክሚላን «ከአፍሪቃ የለዉጥ ነፋስ እየነፈሰ ነዉ።» ማለታቸዉ ማረጋገጪያ ነዉ።ወዲያዉ የሮዴሽያ ገዢዎች ፓርቲዉን አገዱ።ንኮሞ ግን አላረፉም።

የዚምባቡዌ አፍሪቃዉያን ሕዝብ ሕብረት (ZAPU) ፓርቲን እና የዚምባቡዌ ሕዝባዊ አብዮታዊ ጦር (ZPRA) ያሉትን ወታደራዊ ክንፉን መሠረቱ።1961።ሙጋቤ የፓርቲዉን የምክትል ፕሬዝዳትነት፥ የዋና ፀሐፊነት፥ የዉጪ ግንኙነት የመሳሰሉትን ትልላልቅ ሥልጣኖች ቀርቶ የሕዝብ ግንኙነት ሥልጣኑን እንኳን ብቻዉን ለመያዝ አቅሙ፥ እዉቅናዉ፥ ብስለቱም አልነበዉም።

በሶቬት ሕብረት የሚደገፉት ንኮሞ እንደነ ሌሊኒን የገጠሩን የትጥቅ ትግል ከከተማ ሕዝባዊ አመፅ ጋር የማቀናጀት ሥልታቸዉን የሚቃወሙት የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝዳት ንዳባኒኒግ ሲቶሌ፥ እነ ኤድጋር ቴኬሬ፥ እነ ሊዮፖልድ ታክዋዊራን አስከትለዉ ZANU-የዚምባቡዌ አፍሪቃዉያን ብሔራዊ ሕብረት የተሰኘዉን የቻይኖቹን የገበሬዎች የትጥቅ ትግል መርሕን የሚከተለዉን ቡድን ሲመሰርቱ ሙጋቤም አሮጌ የፖለቲካ መምሕራቸዉን ጥለዉ ካዲሶቹ-አዲስ ፓርቲ ወገኑ።1963።ወዲያዉ ግን ሁሉም ታሰሩ።

በ1979 ብሪታንያ በጠራችዉ ድርድር ላይ ሙጋቤ ከንኮሞ ጋር ግንባር ፈጥረዉ ተካፍለዉ ነበር።በነፃነት ማግሥት ብሪታንያ ጠጋ-ጠጋ ሥታረጋቸዉ እያን የነፃነት ትግል አጋር ወዳጃቸዉን «ጠላት» ለማድረግ ይገፏቸዉ ገቡ።


የያኔዉ የታንዛኒያ ፕሬዝዳት ጁልየስ ኔሬሬ (ለሽምግልና) መጀመሪያ ንኮሞን ቀጥሎ ጠቅላይ ሚንስትር ሙጋቤን ዳሬ ሠላም ቤተ-መንግሥት ጋበዟቸዉ።«ያ ወፍራም ዲቃላ ከተቀመጠበት ወንበር ይቀመጣል ብለሕ አስበሕ ከሆነ፥ እንደገና ማሰብ አለብሕ» አሏቸዉ።ወዲያዉ ከሥነ-ሥርዓታዊ ዉጪ ምንም ሥልጣን የሌላቸዉን የፕሬዝዳት ንኮሞ ደጋፊዎችንና ማታቤሌ-ላንድ በተሰኘዉ ግዛት የሚኖረዉን የንኮሞ ጎሳ የንደቤላ ተወላጆችን አስጨፈጨፉት።1983 ።ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዉ ተገደለ።
                 
«በተለይ ከማታቤሌላንድ ጭፍጨፋ በሕዋላ እና ከዚያ በሕዋላ ለሠላሳ ዓመት በሰፈነዉ ሙስና ምክንያት (ሥልጣን ለሙጋቤ) ከምንም በላይ የሕልዉና ጥያቄ ነዉ።ለዚሕ ነዉ ምርጫዉ ለሳቸዉና ለተከታዮቻቸዉ በጣም ወሳኝ የሆነዉ»

ይላሉ የፖለቲካ ተንታኝ ዱሚሳኒ ንኮሞ።ሙጋቤ በናታቸዉ የሾና ጎሳ አባል ናቸዉ።ሠበቡ ንኮሞ መፈንቅለ-መንግሥት ለማድረግ አሲረዋል የሚል ነበር።ሙጋቤ፥ ከንኮሞ ፓርቲ የተገነጠሉት በንዳባኒንግ ሲቶሌ እና በሊዎፖልድ ታክራዊ ጫንቃ ተንጠልጥለዉ ነበር።በነፃነት ዋዜማ ሁለቱን ለመጣል ከንኮሞ ዳግም ተወዳጁ።

ንኮሞን ለማሽመድመድ የፓርቲያቸዉን ዋና ፀሐፊና የዝነኛዉን ጥቁር ብሔረተኛ የኤድጋር ቴኬሬን ትከሻ ተደግፈዉ ነዉ።ቴኬሬ ንኮሞ ከተሰደዱ በኋላ ከሙጋቤ ጋር የመሠረቱት ጥብቅ መወዳጅነት-እዉነት፥ የሙጋቤ ርዕዮተ ዓለም ተገቢ መስሏቸዉ ሙስና እንዲወገድ፥ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲመሠረት አንድ ሁለት ማለት ሲጀምሩ አሽቀንጥረዉ ጣሏቸዉ።ግን በተቃራኒዉ ንኮሞም ቴኬሬም ሲሞቱ የጀግኖች መታሰቢያ ሐዉልት አቆሙላቸዉ።

በጀርመናዊዉ ቄስ አገላለፅ «ያለፈዉ ዘመን ሰዉ» ያለፈ የትግል የወዳጅ-ጠላቶቻቸዉን ታሪክ በታሪካዊ ሐዉልት መርገዉ ያለፈ-ሥልት ብልሐታቸዉን ባዲሶቹ ተቀናቃኞቻቸዉ ላይ ገቢር ያደርጉ ገቡ።ቀዳሚዉ ሞርጋን ቻንግራይ ናቸዉ።በሁለት ሺሕ ሁለት በተደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እኛ የቀድሞዉ የሠራተኞች ማሕበር ሊቀመንበር ለሙጋቤ የሚያሰጉ አልነበሩም።ሙጋቤ በቀላሉ አሸነፉ።

በሁለት ሺሕ ስምንቱ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ግን አዲሱ ፖለቲከኛ አሮጌዉን መሪ አሸነፉ።ሰዉዬዉ ተንገዳገዱ ግን አልወደቁም።እንዳይወድቁ መጀመሪያ፥-በፀጥታ አስከባሪዎችና በቻንግራይ ደጋፊዎች መካካል በተደረገዉ ግጭት ከሁለት መቶ ባላይ ሰዉ መገደል፥ ቻንጋራይ ሳይቀሩ በመቶ የሚቆጠሩ መደብደብ፥ መቁሰል፥ መታሰር፥ ብዙ ሺሕ መሰደድ ግድ ነበረበት።

ሁለተኛ፥ ሙጋቤ፥ ልክ እነ ንኮሞ፥ እነ ሲቶሌ፥ እነ ቴኬሬ ጠንካራ በነበሩበት ዘመን እንዳደረጉት ሁሉ ካዲሱ ጠንካራ ጠላታቸዉ ጋር መሻረክ ነበረባቸዉ።የያኔዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳት ታቦ ምቤኪ በመሩት ሽምግልና የተደረሰበት ስምምነት በሁለት ሺሕ ዘጠኝ ለቻንግራይ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሥልጣን አሰጥቶ ፀደቀ።
                       
«እኔ ሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ፥ የዚምባቡዌ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳት እርስዎን፥ ሞርጋን ሪቻርድ ቻንግራይ በሕጉ መሠረት ቃላ መሐላ እንዲፈፅሙ እጠይቃለሁ።»

እሳቸዉም ወዳጅነቱን፥ ሥልጣኑንም ተቀበሉ።በቃለ-መሐላ።
                 
«እኔ ሞርጋን ሪቻርድ ቻንግራይ ለዚምባቡዌ በታምኝነት እንደማገለግል፥ የዚምባቡዌን ሕግጋትን እንደማስከብር ቃል እገባለሁ።ፈጣሪ ይርዳኝ።»

የተቀናቃኞቹ መወዳጀት፥ መስማማታቸዉ ለዚምባቡዌ ሕዝብ፥ ለአካባቢዉ ሐገራት፥ ለሰላም ወዳዶች ሁሉ አስደሳች፥ ጥሩ ተስፋ ነበር። ባለፉት አራት ዓመታት የጎላ ሁከት ብጥብጥም አልታየም። የወደመዉ የዚምባዌ ምጣኔ ሐብትም የማንሠራራት ተስፋ አሳይቷል።የአዉሮጳ ሕብረት ጥሎት የነበረዉን የምጣኔ ሐብት ማዕቀብም በአብዛኛዉ አንስቷልም።

ቻንግራይ የሚመሩት MDC ግን ከመጠናከር ይልቅ መሽመድመዱ፥ አንዳድ ባለሥልጣኖቹ ለሕዝብና ለፓርቲያቸዉ ከማሰብ ይልቅ ለግላቸዉ ሐብት ለማጋበስ መጣደፋቸዉ፥ ከሙጋቤ ፈርጣማ ጡንቻ እኩል ለዉድቀታቸዉ ምክንያት ሆኗል።በዚምባቡዌ የጀርመኑ የኮንራድ አደናወር-መታሰቢያ የጥናት ተቋም ባልደረባ ዮርገን ላንገን፥-
                
«የMDC ባለሥልጣናት ብቃት የላቸዉም፥ በየራሳቸዉ ኪስ ገንዘብ አጭቀዋል የሚል ጠንካራ ወቀሳና ትችት ይሰነዘርባቸዋል።በሌላ በኩል ደግሞ ለዉጥ ያመጡ ጠንካራ የምክር ቤት አባላትም አሉ።»

የሞርጋን ቻንግራይ ራሳቸዉ ሴት አዉል ናቸዉ እየተባለ በግል ሕይወታቸዉ ሳይቀር ብዙ ይታማሉ።ሉድገር ሻዶምስኪ የጠቀሰዉ አንድ ለሙጋቤ ፓርቲ የወገነ ጋዜጣ እንደዘገበዉ ደግሞ ቻንግራይ ከፖለቲካ ይልቅ ለሴቶች ሰፊ ጊዜያቸዉን ይሰጣሉ።ከዚሕ ሁሉ በላይ በቻንግራይ ቋንቋ ነብሩ (ሊዮፓርድ) አድፍጠዉ ይጠብቃሉ።
               
«የተሐድሶ ለዉጥ ሳይደረግ ወደ ምርጫ ልንገባ ነዉ።ባነጣጠረበት ከፀና ነብር ጋር ልንጋፈጥ ነዉ።ይሁንና በፈጣሪ ላይ ያለን ዕምነት እና ለዕዉነተኛ ለዉጥ ያለን የጋራ ፍላጎት የተጋረጠብንን ፈተና እንድናሸንፍ ያደርገናል።»

አልሆነም።ተሸነፉ።ሙጋቤ ስልሳ አንድ በመቶ፥ ቻንግራይ ሰላሳ አራት ከመቶ ድምፅ።በምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫም ZANU-PF አብላጫዉን መቀመጫ አግኝቷል።ሞርጋን ቻይንግራይ የምርጫዉን ዉጤት እንደማይቀበሉ አስታዉቀዋል።
                   
«MDC የሐምሌ ሰላሳ-አንዱን ምርጫ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ያደርገዋል።ሀ.በሒደቱ፥ ለ. የተሐድሶ ለዉጥ ባለመደረጉ።»

መፍትሔዉ ቻንግራይ ፍርድ ቤታዊ፥ ፖለቲካዊ፥ ሕጋዊ፥ ዲፕሎማሲያዊ እና ያደባባይ ሰልፍ ይላሉ።የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫዉን ሒደት «ነፃና ፍትሐዊ» ብሎታል።የደቡባዊ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ሳዴክ በምሕፃሩ) «ነፃና ሰላማዊ» ብሎታል። ምዕራባዉያን ሐገራት ከየኤምባሲያቸዉ ባልደረቦች በስተቀር ታዛቢ አልላኩም።ዉጤቱን ግን የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳለዉ አሳሳቢ ብለዉታል።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

epa03809922 Zimbabweans check election results posted outside a polling station in Mbare, Harare, Zimbabwe, 01 August 2013. Prime Minister Morgan Tsvangirai on 01 August declared Zimbabwe's general election to be 'null and void' due to allegations of vote rigging and warned the country was on the brink of a crisis. The country's most important independent network of election observers announced it too doubted the legitimacy of the ballot. The 89-year-old Zimbabwean president, Robert Mugabe, who has been at the helm of the country since 1980, has vowed to step down if he is declared the loser in the election. EPA/AARON UFUMELI +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa
Prime Minister of Zimbabwe Morgan Tsvangirai addresses a media conference in Harare on August 3, 2013 Zimbabwe President Robert Mugabe's party claimed Friday it was headed for victory in crunch elections branded a 'sham' by his rivals as international observers prepared to hand down their verdict Friday. A leading opposition figure called for 'passive resistance' over the outcome of Wednesday's presidential and parliamentary elections, which the opposition and local monitors charge was riddled with flaws. AFP PHOTO / ALEXANDER JOE (Photo credit should read ALEXANDER JOE/AFP/Getty Images)
ምስል Alexander Joe/AFP/Getty Images
epa03812296 Zimbabwe Electoral Commission (ZEC) Chairperson Rita Makarau announces the presidential vote results at a local hotel in the capital, Harare, Zimbabwe, 03 August 2013. Zimbabwe's incumbent President Robert Mugabe won a seventh term in office according to officials. Presidential candidate prime minister Morgan Tsvangirai claimed the elections for parliament and president were fraudulent and promised legal action. EPA/AARON UFUMELI
የምርጫ ኮሚሽን ሐላፊ -ሪታ ማካራዉምስል picture-alliance/dpa
HARARE, Aug. 3, 2013 (Xinhua) -- The file photo taken on July 30, 2013 shows Robert Mugabe attending a press conference about the general election at the State House in Harare, capital of Zimbabwe. The Zimbabwe Electoral Commission announced on Aug. 3, 2013 that presidential candidate of Zimbabwe African National Union-Patriotic Front (Zanu-PF) Robert Mugabe won the presidency. (Xinhua/Meng Chenguang) XINHUA /LANDOV
ምስል picture alliance / landov

ነጋሽ መሐመድ

ሽዋዬ ለገሠ









 





 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ