1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓይነ ስውራንን የሚመለከተው ስብሰባ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 28 2011

የዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር እና የአፍሪቃ የዓይነ ስውራን መድረክ ከግማሽ ዓመት በኋላ ለሞካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ላይ ጥሪ አስተላለፉ።

https://p.dw.com/p/3GP1z
Äthiopien International Blinds Association Forum  in Addis Abeba
ምስል DW/G.T. Hailegiorgis

ከስድስት ወራት በኋላ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የዓይነ ስውራን ማህበር ጉባኤ የኢትዮጵያ የዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር እና የአፍሪቃ የአይነ ስውራን መድረክ ከወዲሁ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ላይ ሁሉን አቀፍ ጥሪ አስተላልፈዋል። የህግ ባለሙያ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ዓይነ ስውራንን በሚመለከት ብዙ ተግዳሮቶች ያሉባት ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል። ኢሊሊ ሆቴል የተካሄደውን ስብሰባ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሏል።

 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ