1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓሣ ዓይነቴዎች በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2003

በኢትዮጵያ ከአንድ መቶ ሰማንያ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱ የዓሣ ዓይነቴዎች መኖራቸዉን ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ።

https://p.dw.com/p/RHQY
ምስል RIA Novosti

በመላዉ ዓለም ደግሞ ከ35ሺ በላይ የዓሣ ዓይነቶች መኖራቸዉን ይነገራል። በአገሪቱ ህዝብ ዘንድ በገበታ ላይ የሚታወቁትና ንግዱም የለመዳችዉ ግን ከሶስት ዓይነት አይበልጡም። ዓሣን መብላት በብልሃት የሚል በአበላል ሂደት ለእሾሁ ሊደረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ የሚያመለክት ብሂል ባለዉ ኅብረተሰብ ዉስጥ በገበታ ላይ የሚታወቁት የዓሣ ዓይነቴዎች ኢትዮጵያ አሏት ከሚባለዉ የዓሣ የብዝሃ ህይወት ስብጥር አንፃር እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም። በሌሎች ሀገራት የአበላል ልማድ ዉስጥ የምናያቸዉን የዓሣ ዘሮች ለመድፈር የቻልን ካለን እኛ ከምናዉቀዉ ዓይነት የተለየዉን የዓሣ ዘር ስናይ ሳንሳቀቅ ልንመገብ እንችላለን።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ