1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስና ሙስና

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2001

የኢኮኖሚ ቀውስ ዓለማችንን ባናጋበት በአሁኑ ወቅት በንግዱ ዓለም በተለይ በግሉ ዘርፍ ጉቦ መስጠት እያደገ መምጣቱን አገራት የሚገኙበትን የሙስና ደረጃ የሚያጋልጠው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት አስታወቀ

https://p.dw.com/p/I2vB

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሊቀመንበር Huguett Labelle ዛሬ እንዳስታወቁት በአሁኑ ጊዜ በተለይ በቅርቡ ነፃነታቸውን በተጎናፀፉ አንዳንድ አገራት ባለሀብቶች የሚፈልጉትን ለማግኘት ለመንግስት ባለስልጣናት ጉቦ መስጠት መገደዳቸው አንዱ ትልቁ ችግር ሆኖ ተገኝቷል ። ባለሀብቶች ብቻ ሳይሆኑ ድሀው ህብረተሰብም የተለያዩ አገልግሎቶች ለማግኘት ከቀድሞው ይልቅ አሁን ጉቦ በመስጠት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል ።

ሂሩት መለሰ / አርያም ተክሌ