1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የንግድ ድርጅት

ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2008

የዓለም የንግድ ድርጅት በሃገራት መካከል የሚካሄዱ የንግድ እንቅስቃሴዎች ደንቦች የሚመለከተው ብቸኛው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ነው። ድርጅቱ መንግሥታት የንግድ ስምምነቶች ላይ ድርድር የሚያካሂዱበት ብቻ ሳይሆን በንግድ አማካይነት የሚከሰቱ ግጭቶች መገላገያ መድረክም ነው።

https://p.dw.com/p/1JTwe
Symbolbild Europa Wirtschaft Export
ምስል Fotolia

[No title]


ከዚህ ሌላ አባል ሃገራት በዋነኝነት ለሚያጋጥሟቸው ከንግድ ጋር ለተያያዙ ችግሮች መፍትሄ የሚፈልጉበትም መድረክ ነው ። የድርጅቱ ዓላማ የሸቀጦች አምራቾችን ፣ አገልግሎት ሰጭዎችን እንዲሁም በገቢ እና ወጪ ንግድ የተሰማሩትን መርዳት ነው ።የዶቼቬለው ዌንክል ሮልፍ እንደዘገበው ተፈላጊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሄደው ዓለም ዓቀፉ የንግድ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር WTO ስጋቶችም አሉት ።
የዓለም የንግድ ድርጅት ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት በምህፃሩ IMF እና ከዓለም ባንክ ጎን ከተመ ማዕከላዊ ድርጅቶች አንዱ ነው ።መቀመጫውን ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ያደረገው ይኽው ድርጅት በአሁኑ ጊዜ 162 አባል ሃገራት አሉት ።ከመካከላቸውም ሁለት ሶስተኛ ያህሉ የያደጉ ወይም በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ናቸው ። የድርጅቱ አባላት ከዓለም ንግድ 97 በመቶውን ያንቀሳቅሳሉ ።በአሁኑ ጊዜ 20 ሃገራት የታዛቢነት ቦታ ያገኙ ሲሆን የድርጅቱ አባል ለመሆን ድርድር እያካሄዱ ነው ።ሃገራት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነው ።የመጨረሻ ዙር ትልቁ ድርድር የሚካሄደው እና የሚጸድቀወውም በዶሃው መድረክ ሲሆን ምን ጊዜም ቢሆን የመጨረሻው ትክክለኛው ግብ ላይ ተደርሶ አይታወቅም ። በዶሃ ያልተሳኩ ድርድሮች በዓለም የንግድ ድርጅትም አይሳኩም ።በርግጥ በዓለም የንግድ ድርጅት ብዙ ሃገራትን ከሚያካትቱ የንግድ ስምምነቶች ይልቅ በርካታ አነስተኛ አካባቢያዊ እና የሁለትቶሽ ስምምነቶች መፈረማቸው የሚያጠያይቅ ነው ።ሆኖም በጀርመን የልማት ፖሊሲ ጥናት ተቋም የንግድ ጉዳዮች አዋቂ ካርላ ብራንዲ በአሁኑ ጊዜ የድርጅቱ ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ ።
«የዓለምየንግድ ድርጅት አሁንም አባል ለመሆን የታጩትን እና ላይቤርያ እና አፍጋኒስታንን የመሳሰሉትን ሃገራትም የሚስብ ድርጅት ነው ። በዘመናዊ የንግድ ስርዓት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የሚያሳዩ ሃገራት ድርጅቱ ውስጥ መግባታቸው የተሻለ የገበያ የሚያገኙበት እድል እንዲጨምር ያደርጋል ። »
ከሦስት ዓመት በፊት በታህሳስ 2013 ዓም 160 የድርጅቱ አባል ሃገራት በኢንዶኔዥያዋ ደሴት ባሊ ተሰብስበው ዓለም ዓቀፍ የሸቀጦች ልውውጥ በሚቀላጠፍበት መንገድ ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።በዚያን ጊዜም የዶሃው ዙር የተሳካ ፍጻሜ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አልነበረም ፤ ይህ ግብ ግን ሊደረስበት አልቻለም ።የንግድ ሚኒስትሮቹ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ወደፊት መራመድ ያልቻለውን አሠራር ለመለወጥ ተስማምተዋል ።ከዚይን ጊዜ ወዲህ ትኩረቱ ከባሊው ሂደት በኋላ ያለው እንቅስቃሴ ላይ ሆኗል ። የባሊው ሰነድ የሸቀጦችን የወጪ እና የገቢ ንግድ ያመቻቻል፤፣የእርሻ ማካካሻዎች እንዲቀንሱ ያደርጋል፤፣እንዲሁም ዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሃገራትን የወጪ ንግድ እድሎች ያሻሽላል ።ከስምምነቱ የሚጠበቀውም እድገትን እውን ማድረግ እና የሥራ እድሎችን መፍጠር ነው ።የመስኩ ባለሞያዎች እንደሚሉት ቀረጥ እና የንግድ ወጪ በአንድ በመቶ ብቻ እንኳን እንዲቀንሱ ቢደረግ በማደግ ላሉ ሃገራት ወደ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተ,ጨማሪ ገቢ ሊያስገኝ ይችላል ።የባሊው ስምምነት ዋናው ተግባሩ የዓለም የንግድ ድርጅት በአባል ሃገራት መካከል መተማመንን እንዲያሰፍን ማደረግ ነው ።
የዓለም የንግድ ድርጅት በመደራደሪያ መድረክነቱ ቀውስ ውስጥ ይገኛል ።ሆኖም ድርጅቱ የመደራደሪያ መድረክ ብቻም አይደለም ። ሌሎች ጠቃሚ ተግባራትም አሉት ።እነዚህንም በሚገባ ተወጥቷል ይላሉ የጀርመን የልማት ተቋም ባልደረባ ክላራ ብራንዲ
«ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ዓለም ዓቀፍ ደንቦች እየሰሩ ነው ።የዓለም የንግድ ድርጅት ደንቦች ከዓለም ዓቀፉ የፋይናንስ እና የኤኮኖሚ ቀውስ በኋላም ጥበቃ እና ቁጥጥር አካተዋል ።»
የዓለም የንግድ ድርጅት ከምንም በላይ በንግድ ምክንያት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ረገድ ስኬታማ ነው ።ግጭቶች የሚፈቱበት ደንቦች እና ሂደቶች መግባባያ ሰነድ ከዓለም የመጀመሪያው አሳሪ ዘዴ ነው ። የድርጅቱ አባላት በሰነዱ የተካተቱትን ግጭቶች የሚፈቱባቸውን ደንቦች ለመቀበል ተስማምተዋል ።በጎርጎሮሳዊው 2014 መረጃ መሠረት ከ1995 ዓም አንስቶ ከ470 በላይ የሚሆኑ አለመግባባቶች ለድርጅቱ ቀርበዋል ።ከመካከላቸው አብዛኛዎቹ ምክክር በሚባለው ደረጃ ላይ ተፈተዋል ። ያም ሆኖ አሁን ወደፊት ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ላይ ያሉት ሃገራት ወደፊት ሊወስዱ የሚችሉት እርምጃ ከወዲሁ አሳሳቢ ሆኗል ። እነዚህ ሃገራት ከዓለም የንግድ ድርጅት ወጥተው የራሳቸውን አካባቢያዊ ድርድር እንዳይጀምሩ ያሰጋል ።ሆኖም ብዙ ሃገራትን የሚያቅፉ ስምምነቶች ግን አስፈላጊ ሆነው መዝለቃቸው አያጠራጥርም ። በክላራ ብራንዲ አስተያየት የዓለም የንግድ ድርጅት ሁሉም ድምፁን ማሰማት የሚችልበት መድረክ ነው ።
«አድሎ እንደሚደርስበት ለሚሰማው ለማንኛውም አባል ሃገር እንደ ላይቤሪያ እና አፍጋኒስታን ላሉት አገሮች ጨምሮ ሂደቱ ክፍት ነው ። የዓለም የንግድ ድርጅቶች ድክመቶች ሊኖሩት ይችላሉ ።ሆኖም ድርጅቱ ሁሉም አባል ሃገራት በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡበት እና ድምፃቸውም የሚሰማበት መድረክ ነው ።»
ብዙ ሃገራትን የሚያቅፉ ስምምነቶች በስምምነቱ ውስጥ ያልተካተቱትን አያገሉም ።ይልቁንም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ገዥ ኃይል ያላቸው ደንቦች ይኖሩዋቸዋል ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Kenia WTO Treffen in Nairobi
ምስል Reuters/N. Kharmis
Logo Welthandelsorganisation WTO