1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የዓለም ንግድ ድርጅት ሥራ እና አሠራር

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 18 2010

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ለድሆች የሚቆረቆሩ ተቋማት እና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች ዓለም አቀፉ ድርጅት የመሥራቾቹን የምዕራባዉያንን ፍላጎት እና ጥቅም ለማስከበር የቆመ ነዉ ይላሉ

https://p.dw.com/p/2q0ph
Logo Welthandelsorganisation WTO

Wirtschaft (271217) WTO-Pro und Contra - MP3-Stereo

 የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) ዓላማ እና አሠራር ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ወገኖችን እንዳከራከረ ነዉ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ለድሆች የሚቆረቆሩ ተቋማት እና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች ዓለም አቀፉ ድርጅት የመሥራቾቹን የምዕራባዉያንን ፍላጎት እና ጥቅም ለማስከበር የቆመ ነዉ ይላሉ። የምዕራቡን ዓለም የምጣኔ ሐብት መርሕ የሚያቀነቅኑ ባንፃሩ ዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት ለድሆችም፤ ለበለፀጉትም ሐገራት ሕዝብ እኩል ጠቃሚ ነዉ ባይ ናቸዉ። የዛሬዉ ከኤኮኖሚዉ ዓለም ዝግጅታችን ክርክሩን ባጭሩ ይቃኛል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ነዉ ያዘጋጀዉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ