1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ሴቶች ቀን

ሐሙስ፣ መጋቢት 6 2004

ዓለም አቀፍ የሴቶች እኩልነት ዕለት (ማርች ስምንት) ዛሬ በመላዉ ዓለም በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ታስቦ ዉሏል።የዓለም ሴቶች ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም፡ የሴቶች እኩልነትም ሆነ ሴቶች በፆታቸው ሰበብ የሚደርስባቸው አድልዎ ጨርሶ አለተወገደም። ይህ ገሀድ እስኪሆን ድረስ

https://p.dw.com/p/14HW2
የሴቶች መብት ጥያቄምስል picture-alliance/dpa Fotografia

ገና ብዙ ጊዜ እንደሚቀር የሴቶች መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። እርግጥ፣ የዓለም ሴቶች ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም፡ የሴቶች እኩልነትም ሆነ ሴቶች  በፆታቸው ሰበብ የሚደርስባቸው አድልዎ ጨርሶ አለተወገደም። ይህ ገሀድ እስኪሆን ድረስ ገና ብዙ ጊዜ እንደሚቀር የሴቶች መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። የወንዶች ተፅዕኖ አሁንም ጎልቶ በሚታይበት ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ከደረሱት ሴቶች መካከል አንዷ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ናቸው፤ የሜርክልን ጉዞ የተከታተሉት ደራሲዋ ዣክሊን ቦይዘን እንደሚሉት፡ ብዙዎች ሜርክል ከፍተኛ ሥልጣን ይይዛሉ የሚል ግምት አልነበራቸውም። አርያም ተክሌ

ጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከፍተኛ ቦታ ይደርሳሉ ተብለው ከማይጠበቁት የሀገሪቱ ፖለቲከኞች መደዳ ነበር የተቆጠሩት። እአአ ከ 1945 ዓም በኋላ በታየው የጀርመን ታሪክ ውስጥ ከምሥራቃዊው የጀርመን ክፍለ ሀገር ከወንጌየቄስ የተወለዱትን ልጅ ያህል የተናቀ አንድም ፖለቲከኛ የለም። ይህን ሜርክል ገና መራሒተ መንግሥት ሳይሆኑ ገና ስለርሳቸው የሕይወት ታሪክ መጽሓፍ ያሳተሙት ወይዘሮ ዣክሊን ቦይሰን ያረጋግጣሉ።
« እርግጥ አንጌላ ሜርክል ርዕዮተኛ አይደሉም። በቁጥር፡ በመረጃ እና በገሀድ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ውሳኔ ለመውሰድ ነፃ ናቸው። አስፈላጊ በሚሆንበትና አሳማኝ መከራከሪያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ፡ ሜርክል በተለያዩ የፖለቲካ መስኮች ላይ፡ ርዕዮት ዓለምን ወደኋላ በመተው ወይም በመርሀግብር መመሪያዎች ሳይገድቡ የአቋም ለውጥ አሳይተዋል። »
ይህ አሰራራቸው አልጎዳቸውም። እንዲያውም፡ በአንጻሩ የኮል ጥገኛ እየተባሉ በምፀት ይጠሩ የነበሩት ሜርክል አሁን ተወዳጅና ራሳቸውን የቻሉ ጠንካራ መሪ ለመሆን በቅተዋል። የአንድ የወንጌላዊ ቄስ የመጀመሪያ ልጅ የሆኑት አንጌላ ዶሮቴአ ካዝነር ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሲሆን፡ በላይፕሲኽ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ትምህርታቸውን በጣም ጥሩ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል። ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሳሉ ከትምህርት ጓዳቸው ኡልሪኽ ሜርክል ጋ ትዳር በመመሥረት የባለቤታቸውን መጠሪያ ስም ያዙ፡ ግን ብዙም ሳይቆዩ ቢፋቱም ሜርክል የሚለውን ስም እንደያዙ መቆየቱን መርጠዋል። ሜርክል በቀድሞዋ ዲዲአር ውስጥ የመንግሥት ተቃዋሚ አልነበሩም፤ ግን አንዳንድ ---አላጋጠማቸውም ማለት አይደለም። እንደዚያም ቢሆን  ቦይዘን እንደሚሉት፡ሶሻሊስታዊትዋ ሀገር በብዙዎቹ ተቃዋሚዎች ላይ ያደረሰችው በደል አልደረሰባቸውም። የልጅነት ጊዜያቸው ጥሩ እንደነበር ነው ሜርክል የሚናገሩት።
ወደ ፖለቲካው መስክ ዘግይተው የገቡት ሜርክል በሠላሣ አምስት ዓመታቸው  የቀድሞዋ ዲዲአር የመጨረሻ ጠቅላይ ሚንስትር ምክትል የፕሬስ ቃል አቀባይ ሆኑ፤ ከዚህ ጥቂት ቀደም ሲል የክርስትያን ዴሞክራቶቹ ህብረት ፓርቲ አባል የሆኑት ሜርክል በ1990 ዓም በተዋሀደች ጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት እንደራሴ፡ ከዚያም መራሒ መንግሥት ሄልሙት ኮል ሳይታሰብ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ሚንስትር አድርገው ሾሙዋቸው። ያኔ ሜርክል ይህን ቦታ ያገኙት ወጣት፡ ሴትና ከምሥራቅ ጀርመን በመምጣታቸው ብቻ የሚል ወሬ ተናፍሶ ነበር። በ 1994 ዓም የተፈጥሮ ጥበቃ ሚንስትርእንደኑም የምክትልነቱን ቦታ ይዘው የነበሩትን ባለሥልጣን አንስተው የራሳቸውን ሰው በሰየሙበት ጊዜ፡ የመገናኛ ብዙኃን ይህ ደፋር የሜርክል ርምጃ በብዛት በወንዶች በተያዘው የፖለቲካ መድረክ ውስጥ ያሳደሩትን በራስ መተማመናቸውንና ጥንካሬአቸውን ያሳየ ነው በሚል አረጋግጠውላቸዋል።   ሜርክል የማድመጥ እና ከፍ ያለ የመግባባት ችሎታ እንዳላቸው የፓርቲ ጓዶቻቸው ቢያረጋግጡም፡ ይኸው የሲዲዩ ሊቀመንበር የሆኑት የሜርክል ፈጥኖ የማገናዘብ ችሎታ አልተዋጠላቸውም።
« መናገር ከተፈቀደለኝ፡ ሴትዮዋ ጉዳዮችን ያዳምጣሉ፤ ያገናዝባሉ፤ ሂደቶችን በሚገባ ይረዳሉ፤ ይሁን እንጂ፡ ስለሚቀርብላቸው ሀሳብ የሚሰጡት አስተያየት በግልጽ ስለማይታወቅ ውጤቱን ለማወቅ አዳጋች ነው። »
ሜርክል ችግሮችን ፈጥነው የሚያውቁ፡ ውሳኔ ለመውሰድ ግን የሚዘገዩበት ባህርያቸው የሚከተሉት አውታር መለያ ምልክት ነው። ሜርክል ስለራሳቸው ሲናገሩም በርግጥ ተቻኩለው ውሳኔ እንደማይወስዱ ገልጸዋል። አጠቃላዩን ሂደት ተከታትለው መጨረሻ ላይ ነው ውሳኔ የሚወስዱት።  
ሚያዝያ 2000 ዓም ላይ አዲሷ የክርስትያን ዴሞክራቶቹ ህብረት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ በኋላ በ 2005 ዓም በሀገሪቱ በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ፓርቲያቸው በጠባብ የድምፅ ብልጫ በማሸነፉ ከዚያን ጊዜ ወዲህ የመራሒተ መንግሥትነቱን ሥልጣን ይዘው ጀርመንን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

Merkel, spätere Bundeskanzlerin, beugt sich während des CDU-Parteitags in Dresden zu ihrem Mentor Bundeskanzler Kohl
ምስል picture-alliance/dpa
Deutschland Angela Merkel Bundestag Abstimmung Griechenland-Hilfspaket II
ምስል dapd

ዩሐንስ ገብረ እስግዚአብሔር

አርያም ተክሌ/ቫግነር ፈልከር

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ