1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ማህበራዊ መድረክ ውይይት

ዓርብ፣ ጥር 22 2001

ዕውቀታችን ከትምህርት ቤት አለያም ከዩኒቨርሲቲ የተገኘ አይደለም። ከቀደሙ አባቶቻችን የተቀዳ እንጂ። ደናችንን፣ ጅረቶቻችንን እንንከባከባለን። ያም እንዴት እንደሆነ እናውቅበታለን። ከተፈጥሮ ጋር ተጣጥመን ነው የምንኖረው። ተፈጥሮን አናቃውስም። ሌሎች ህብረተሰቦች ያን ያደርጉ ይሆናል፤ እኛ ነባር የህንድ ጎሳዎች ግን አናደርገውም።

https://p.dw.com/p/Gk7q
የአማዞን ደን
የአማዞን ደንምስል AP
ሰሞኑን ቤሌም ብራዚል ውስጥ በተያዘው የዓለም ማህበራዊ መድረክ ውይይት ላይ ከላቲን አሜሪካ የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር አሜሪካውያንና ከተለያየ ቦታ የመጡ የነባር ነዋሪዎች ተወካዮች መገኘታቸው ታውቓል። በሰሜን ብራዚል የአማዞን ክልል በሚገኘው የውይይት ስፍራ የአህጉሪቱ ተወላጆች የተሰባሰቡትበአለም ላይ የተከሰተውን የምጣኔ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግ ነው ።