1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውሀ ችግር በመልማት ወደኋላ በቀሩ ሀገራት

ማክሰኞ፣ የካቲት 2 2002

ከተባበሩት መንግስታት የምዕተ ዓመቱ ግቦች አንዱ ንፁህ የመጠጥ ውሀን ለህዝቡ ማዳረስ ነው ። ይሁንና ድርጅቱ በዚሀ ረገድ በንፁህ የመጠጥ ውሀ ዕጥረት የሚሰቃዩትን የዓለማችንን ህዝቦች ቁጥር በግማሽ ለመቀነስ ያለመ ቢሆንም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንደታሰበውመሳካቱን በርካታ የመስኩ ምሁራን ይጠራጠራሉ ።

https://p.dw.com/p/LxLm
ምስል Isabel Schlerkmann

በአሁኑ ሰዓት ለዚሁ ዓላማ ሲባል ከዓለም ዓቀፍ የልማት ዕርዳታ ገብዘብ አብዛኛው ለውሀ ፕሮጀክቶች ይውላል ። በ Witten-Herdecke ዩኒቨርስቲ የተካሄደ አንድ ጥናት በደረሰበት መደምደሚያ መሰረት ግን በዘርፉ ከገንዘብ ችግር ይልቅ የሙያ ብቃት ዕጦት ጎልቶ ይታያል ። ዝርዝሩን የዶይቼቬለው Klaus Deuse አሰናድቷል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ