1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 22 2013

የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ እንዳሉት መንግስታቸዉ አቋሙን ለዓለም አቀፉ ድርጅት የፖለቲካ እና የሠላም ጉዳዮች ኃላፊ አስረድቷል።ከሳውዲ አረቢያ በሁለት ሳምንት ውስጥ ምንም ዝግጅት ሳይደረግ የአገሪቱ መንግሥት በፈጠረው ጫና የተመለሱ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ወደየአካባቢያቸዉ መላካቸዉን አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/3yHaw
Äthiopien Botschafter Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ መንግስት፣ተመድ፣ሳዑዲ አረቢያና ሱዳን


የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀዉን የተናጥል ተኩስ አቁም ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አለመቀበሉን በተመለከተ ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ማብራሪያ መስጠትዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ እንዳሉት መንግስታቸዉ አቋሙን ለዓለም አቀፉ ድርጅት የፖለቲካ እና የሠላም ጉዳዮች ኃላፊ አስረድቷል።አምባሳደር ዲና እንዳሉት ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ በያዘችው ቦታ ላይ ሰዎችን የማስፈርና ድልድዮችን የመገንባት ተግባር ውስጥ መግባቷን አረጋግጠው ፣ ይህ ድርጊታቸው እንደማያዋጣቸው እየተነገራቸው መሆኑንም ገልፀዋል።ከሳውዲ አረቢያ በሁለት ሳምንት ውስጥ ምንም ዝግጅት ሳይደረግ የአገሪቱ መንግሥት በፈጠረው ጫና የተመለሱ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ወደየአካባቢያቸዉ መላካቸዉን አስታዉቀዋልም።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ