የዉብሸት መሸለምና እንድምታዉ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 6 2006ማስታወቂያ
በእሥር ላይ የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ዉብሽት ታዬ የአሜሪካዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ CNN የሚሠዉን ሽልማት ማግኘቱ ለኢትጵዉያን ነፃ ጋዜጠኞች በሙሉ አበረታች እንደሚሆን ሸላሚዎችና ጋዜጠኞች አስታወቁ።የCNN ባለሥልጣናት እና የቀደሞዉ የዉብሸት ባልደረባ ዳዊት ከበደ በየፊናቸዉ እንዳሉት ሽልማቱ የአፍሪቃን ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሐንን ብቃትና ነፃነት ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ዉብሸት በአሸባሪነት እከታሠረበት ጊዜ ድረስ ኋላ የተዘጋዉ የአዉራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ ነበር።የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ