1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወባ ክትባት ተስፋ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2007

በዓለማችን የ3,2 ሚሊዮን ሕዝብ የጤና ስጋት ነዉ። በየዓመቱም እስካሁን ግን ምንም ዓይነት የመከላከያ ክትባት አልተገኘለትም። በዚህ በሽታ ምክንያት ከሚጠፋዉ ሕይወት ዘጠና በመቶዉ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። ወባ በትንሿ ፍጥረት በትንኝ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ። ሰሞኑን ተስፋ ሰጪ ዜና እየተነገረለት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1G6ZF
Malaria Impfung Afrika Kenia
ምስል AP

በትንሿ ፍጥረት በትንኝ አማካኝነት የሚመጣዉና ተላላፊ የሆነዉ የወባ በሽታ በዓለም ወደ3,2 ቢሊዮን ሕዝብ እያሳቀቀ ሲኖር ዓመታት እንደዋዛ አልፈዋል። ወባ የምታሰቃየዉ ብቻ ሳይሆን የምትቀጥፈዉ የሰዉ ቁጥር መበርከቱም ለበሽታዉ መፍትሄ እንዲፈለግ የግድ ትኩረትም እንዲሰጡ አድርጓል። ለዚህም ነዉ በተመድ የአምዓቱ የልማት ግብ ዉስጥ መዳንና መከላከል ሲቻል የሰዉ ሕይወት ከሚነጥቁ በሽታዎች ተርታ ተመድባ በተቀናጀና ከፍተኛ ዘመቻ ጉዳቱን ለመቀነስ የተወጠነዉ። እርግጥም ዉጥኑ ለዉጥ ማምጣቱን በየዓመቱ የሚወጣዉ መረጃ ያመለክታል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለዉ ከጎርጎሪሳዊዉ 2000ዓ,ም ወዲህ በመላዉ ዓለም በወባ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር በ47 በመቶ ቀንሷል። አፍሪቃ ዉስጥ ብቻ ደግሞ ወደ54 ከመቶ ወርዷል። ያም ሆኖ በዚሁ የዘመን ቀመር 2013ዓ,ም ላይ 198 ሚሊዮን የወባ ታማሚ እንደነበር ተመዝግቧል። የሞቱትም 584 ሺህ ናቸዉ። ይህም ዛሬም ወባ ገዳይና ስጋት መሆኗልን በግልፅ ያመለክታል።

የዓለም የጤና ድርጅት ለዚህ በሽታ መከላከያ የሚሆን ክትባት የመፈለጉን ተግባር እጅግ ዉስብስብ እና በጣም አስቸጋሪ ይለዋል። ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ክትባት ለማግኘት የተካሄዱ ሙከራዎች ቢኖሩም እስካሁን አለመሳካቱንም አልሸሸገም ድርጅቱ። ወደ20 የሚሆኑ የቅመማ ዉጤት የሆኑሊሆኑይችላሉየተባሉ ክትባቶችምበተለያዩአካባቢዎችሙከራላይመሆናቸዉንምአመልክቷል።የወባሰለባዎችምበድሀሃገራትየሚኖሩሕዝቦችናቸዉ።የዓለምየጤናድርጅትእንደሚለዉየዛሬሁለትዓመትበወባምክንያትከጠፋዉየሰዉሕይወት90 ከመቶዉ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። ከእነዚህ መካከልም እድሜያቸዉ ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናት ይበረክታሉ።

ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ ላይ የአዉሮጳ ኅብረት የመድሃኒት ቁጥጥር ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ያለዉ ሞስኩዩሪክስ የተሰኘዉ ክትባት በዚህ በሽታ ገና በለጋ እድሜያቸዉ ለሚቀጠፉት ሕፃናት ተስፋ ሊሆን ይችላል ነዉ የተባለዉ። ክትባት የመገኘቱ ተስፋ ሲሰማም ጋና ዉስጥ በወባ ተይዘዉ ከሚሰቃዩ ልጆቻቸዉ ጋር በየሃኪም ቤቱ የሚገኙ በርካታ እናቶች ከወዲሁ እፎይታ ነዉ የተሰማቸዉ። ማምቢ ጀነራል በተሰኘዉ ሃኪም ቤት የሚሠሩት ዶክተር ሳላማታ ናንቶግማ ይህን ስቃይ በቅርብ ያዉቁታል፤

«ከአምስት ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ሕፃናት ሞት በጣም ያሳስበናል። በእዚህ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች ሃኪም ቤት የመግባት ዋናዉ ምክንያት ወባ ነዉ። እናም እጅል ልናተኩርበት የሚገባ የበሽታ ዓይነት ነዉ።»

ልጆቻቸዉ ዶክተሯ በሚሠሩበት ሃኪም ቤት በወባ ምክንያት የተኙ ሕፃናት ወላጆች ከዕለታት አንዱን ቀን ሊረዳቸዉ እንደሚችል የሚታመነዉ ወባን የመከላከያ ክትባትን ለማግኘት የሚደረገዉ ጥረትና ምርምሩ ስለደረበት ደረጃ የሚያዉቁት የለም። ሆኖም ግን ይህን የሚከታተሉት የጋና የህክምና ባለሙያዎች የአዉሮጳ የመድኃኒቶች ክትትል ተቋም ግላስኮ ስሚዝ ክላይን የተሰኘዉ የመድኃኒት ፋብሪካ ለቀመመዉ ክትባት ማረጋገጫ መስጠቱን የሚያበስረዉን ዜና በደስታ ነዉ የተቀበሉት። የጋና የወባ መቆጣጠሪያ መርሃግብር ባልደረባ ዶክተር ኬዝላህ ማልማ፤

«ከዓለም ፈፅመዉ የጠፉ በሽታዎችን ሁኔታ ስንመለከት ክትባቶች ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል። ስለዚህ እኛም ይህ የዚህ ጥረት መጀመሪያ በመሆኑ ተደስተናል። እርግጥ ነዉ የወባ ክትባትን ለማዘጋጀት ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል እናዉቃለን ግን ደግሞ ይህ መነሻዉ በመሆኑ የመጀመሪያዉ መልካም ርምጃ ብለን ተቀብለነዋል።»

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ክትባቱ ጋናና ማላዊን ጨምሮ አፍሪቃ ዉስጥ በ11 የተለያዩ ሃገራት ሲሞከር ቆይቷል። እንደሚታወቀዉ በየዓመቱ በወባ ምክንያት ከሚሞቱት ሕፃናት ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። የሕፃናት አድን ባልደረባ ሲሞን ራይት ክትባቱስ ዉጤት ማሳየቱ መልካም ነዉ ግን ዋጋዉና እንዴትስ ይዳረሳል የሚለዉ አሳስቧቸዋል፤

«የዚህ ክትባት መገኘት እጅግ አስደሳች ነገር ነዉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ዉጤት ያሳየ መሆኑም አንድ ነገር ነዉ። አሁንም ግን በርካታ ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባቸዋል። ዋጋዉ ስንት ይሆናል? እንዴትስ ነዉ የሚዳረሰዉ? ምን ያህል ጊዜስ ይፈጃል?»

እንዲያም ሆኖ የዓለም የጤና ድርጅት የወባ ክትባቱ ሥራ ላይ እንዲዉል ከመምከሩ አስቀድሞ እስከያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 መጨረሻ ድረስ ክትባቱ ያስገኛቸዉን ዉጤቶች መርምሮ ማፅደቅ ይኖርበታል።

ጥናትና ሙከራዎች ለረዥም ጊዜያት መካሄዳቸዉን ያመለከቱት በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ የወባ መከላከልና መቆጣጠሪያ ክፍል ባለሙያ አቶ ደረጀ ድሉ በበኩላቸዉ ይህ ነዉ የሚባል ክትባት መገኘቱ አንድ ነገር ቢሆንም ለፈላጊዎቹ የወባ ተጎጂዎች መቼ ይዳረሳል የሚለዉ ዋና ጥያቄ ነዉ ይላሉ።

እንደታቀደዉ ዉጤታማ ነዉ የተባለዉ የወባ ክትባት በዓለም የጤና ድርጅት እዉቅና ካገኘ ሥራ ላይ ሊዉል የሚችለዉ በጎርጎሪዮሳዊዉ 2017ዓ,ም እንደሚሆን ይጠበቃል። እስከዛሬ ወባን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት መድኃኒት የተነከረ አጎበር እና የተለያዩ መድኃኒቶች የማይናቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ወባን ለመቆጣጠር በሚሠራዊ ሥራ ትርጉም ያለዉ ለዉጥ መመዝገቡን የሚናገሩት አቶ ደረጀ በዚያ ላይ ክትባት መምጣቱ ትልቅ ጥቅም እንደሚሆን አመልክተዋል።

ባለሙያዉ እንደሚሉትም ለወባ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ተጓዳኝ ትችር በማስከተላቸዉ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸዉ በመሆናቸዉ ብቻ ሳይሆን በቀላሉ መላመድ እንዳሲከሰትና ፈዋሽነታቸዉ ጥያቄ ላይ እንዳይወቅድ የሚለዉም ሌላዉ ፈተና ነዉ የሆነዉ። እንደተስፋዉና እቅዱ በአዉሮጳ የመድኃኒት መቆጣጠሪ ተቋም ይለፍ ያገኘዉ ክትባት የዓለም የጤና ድርጅትን ይሁንታ ለማግኘት ጊዜ መዉሰዱ አይቀርም።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ