1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኹዋንታናሞ እስረኞችና አቃቤ ሕጉ

ዓርብ፣ ኅዳር 26 2001

በኹዋንታናሞ እስረኞች ላይ የሚፈፀመዉ በደል እና የምርመራዉ ሒደት የዩናይትድ ስቴትስን የፍትሕና የዲሞክራሲ ሥርዓት የጣሰ ነዉ

https://p.dw.com/p/GA8q
እረኞቹምስል AP

የዩናይትድ ስቴትስ መስተዳድር በአሸባሪነት ጠርጥሮ ኹዋንታናሞ-ኩባ ደሴት ካሰራቸዉ መካካል ሰባቱ የተከሰሱበት የጦር ፍርድ ቤት አቃቤ-ሕግ የነበሩት ኮሎኔል ዳርል ቫንድቨልድ ሰሞኑን ሥራቸዉ በፈቃዳቸዉ ለቀዋል።ኮሎኔሉ ከዚሕ ዉሳኔ የደረሱት በኹዋንታናሞ እስረኞች ላይ የሚፈፀመዉ በደል እና የምርመራዉ ሒደት የዩናይትድ ስቴትስን የፍትሕና የዲሞክራሲ ሥርዓት የጣሰ ነዉ በሚል ተቃዉሞ ነዉ።ኮሎኔል ቫንድቨልድ ጉዳያቸዉን ከያዙት መካካል ብሪታንያ ይኖር የነበረዉ ኢትዮጵያዊዉ ቢንያም መሐመድ አንዱ ነዉ።አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዝር ዝሩን ልኮልናል።