1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮፐንሃገን ተስፋ መደብዘዝ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 8 2002

በኮፐንሃገን የሚካሄደዉ 15ኛዉ የአየር ንብረት ጉባኤ የጨመረዉን የዓለም የሙቀት መጠን መቀነስ ከሚያስችለዉ ስምምነት አይደርስም የሚሉ ስጋቶች እየተሰሙ ነዉ።

https://p.dw.com/p/L6Ob
ተጨባጭ ዉል ጠያቂ ሰልፍምስል AP

ጉባኤዉ በሚካሄድባት ኮፐንሃገን የሚገኘዉ የዶይቼ ቬለዉ ዮሃንስ ቤክ እንደዘገበዉ የተለያየ ሃሳብና ፍላጎት ይዘዉ ዴንማርክ የተሰባሰቡት ወገኖች አያያዛቸዉ ሁሉን በሚያግባባ ዉል የሚታሰር አይመስልም። ትናንት ተሰባስበዉ ከጉባኤዉ በሚጠብቁት ዉሳኔ ላይ የተወያዩት የአፍሪቃ መሪዎችና የመንግስታት ተወካዮችም ከጉባኤዉ የሚፈልጉትን ለማስታረቅ ተቸግረዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ