1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮፊ አናን የሶርያ ጉብኝት

ሰኞ፣ መጋቢት 3 2004

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን የሶሪያው ዓመጽ በፍጥነት እንዲያበቃ፣ የዕርዳታ ድርጅቶች ያላንዳች መሰናክል ወደ ቀውሱ አካባቢዎች መግባት እንዲችሉና የፖለቲካ እስረኞች ነጻ እንዲለቀቁ ቢጠይቁም ፍሬያማ ውጤት እስካሁን አላገኙም።

https://p.dw.com/p/14JVj
have been killed. REUTERS/SANA/Handout (SYRIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
የተባበሩት መንግሥታትና የአረብ ሊግ ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን እና ፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድምስል Reuters

የተባበሩት መንግሥታትና የአረብ ሊግ ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን ትናንት ደማስቆስ ውስጥ ከፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድ ጋ እንደገና ተገናኝተዋል። የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን የሶሪያው ዓመጽ በፍጥነት እንዲያበቃ፣ የዕርዳታ ድርጅቶች ያላንዳች መሰናክል ወደ ቀውሱ አካባቢዎች መግባት እንዲችሉና የፖለቲካ እስረኞች ነጻ እንዲለቀቁ ቢጠይቁም ፍሬያማ ውጤት እስካሁን አላገኙም። ሆኖም አናን ተስፋ እንደማይቆርጡ ነው «የቢይሮን ባላሽከ» ዘገባ የሚያመላክተው።

የተባበሩት መንግሥታትና የአረብ ሊግ ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን በሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ ከሶሪያ ፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድ ጋ ተወያይተዋል። በሁለት ቀን ውስጥ ብዙ የመወያያ ርዕሶች ሊነሱ ይችላሉ ተብሎ ሊጠበቅ ይችላል። ርግጥ ነው። ይሁንና አናን ስለ ተልክዋቸው ሲናገሩ ብዙም ስኬታማ አልነበረም።

« አዎ! ጠንካራ እና ከባድ ነው የሚሆነው። ይሁንና ተስፋ ሊኖረን ይገባል። በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ በጎ አስተሳሰብ አለኝ። ለአጭር ጊዜ ነው እዚህ የነበርኩት። እያንዳንዱ ያገኘሁት ሶሪያዊ ሰላም ነው የሚፈልገው። እዚህ ያሉት ሰዎች አመፁ እንዲያበቃ ነው የሚፈልጉት። ህይወታቸውን እንዲቀጥል ነው ፍላጎታቸው።»

አናን ከፐሬዚዳንት አሳድ ጋ ስላደረጉት አብይ ርዕስ ምላሽ ሲናገሩ ብዙም ተጨባጭ ነገር አልነበረውም። ውይይታችን ያተኮር የነበረው አሉ አናን፤ «ዋናው ነገር ላይ ነው። ይህም ዓመፁ በፍጥነት እንዲያበቃ፣ የዕርዳታ ድርጅቶች ያላንዳች መሰናክል ወደ ቀውሱ አካባቢዎች መግባት እንዲችሉና የሶሪያ መንግሥትና ተቃዋሚዎች ለመነጋገር እንዲችሉ ነው።» አናን ቀጥለው ሲናገሩም። « ፕሬዚዳንቱን አንዳንድ ሀሳብ አቅርቤላቸዋለሁ። ግልፅ የሆኑ ሀሳቦች ናቸው። በተግባር ላይ ከዋሉ በፍጥነት ሊታዩ የሚችሉ ነገሮች። ሂደቱን የሚያሻሽል እና ችግሩን ለመፍታት የሚረዳ ነው።»

Syria's President Bashar al-Assad (centre R) meets U.N.-Arab League envoy Kofi Annan (centre L) in Damascus March 10, 2012, in this handout photograph released by Syria's national news agency SANA. Annan arrived in Damascus on Saturday to press President al-Assad for a political solution to Syria's year-long uprising and bloody crackdown in which thousands of people have been killed. REUTERS/SANA/Handout (SYRIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ምስል Reuters

የተባበሩት መንግሥታትና የአረብ ሊግ ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን እንደሚሉት የሶሪያን አመፅ የሚያስቆም ስምምነት ወይም ውል ለመፈራረም ገና የማይታሰብ ነው። ይሁንና አናን ለ2ኛ ጊዜ ከአሳድ ጋ ያደረጉት ውይይት ከመጀመሪያው ጋ ሲነፃፀር የተሻለ ነው። አናን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሳድ ጋ ከተገናኙ በኋላ አሳድ ለአገራቸው የዜና ወኪል SANA ሲገልፁ « የተስተካከለ አመራር በአገሪቱ እንዳይኖር የሚጥሩ የታጠቁ አማፂያን እስካሉ ድረስ ማንኛውም ንግግር ስኬታማ ቢስ ነው። » አሳድ አማፂ ሲሉ የሚጠሩት የሶሪያን መንግስት በመቃወም በአጠቃላይ የታጠቀውን የአገሪቷን ወገን ነው።

አናን ሶሪያን በጎበኙበት ወቅት የሶሪያ መንግሥት ጦር በአገሪቱ ሰሜንዊ ክፍል-ሐገር በኢድሊብ በተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ሲያደርስ ነበር። በአንፃሩ የሶሪያ ነፃ ውጪ ግንባር በመጠኑም ቢሆን በኢድሊብ በነበረው ውጊያ ስኬታማ እንደሆነ ለአልጃዚራ ገልጿል። « አንድ ሄሊኮፕተር እና ስድስት መድፎችን ልንመታ ችለናል ሲሉ የቡድኑ ተጠሪ ራሲድ አል አሳድ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሶሪያ ዜጎች ወደ ቱርክ ደንበር እየተሰደዱ ነው። የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ኮፊ አናን በሶሪያ የነበራቸው ውይይት እንደተጠበቀው ፈጣን መፍትሄ አያስጊኝ እንጂ፤ አሳድ በፊት ለፊት ለምንም አይነት ድርድር ዝግጁ እንዳልሆኑ ለመናገር ካልደፈሯቸው ሰዎች አንዱ ኮፊ አናን ናቸው።

A family escapes from fierce fighting between Free Syrian Army fighters and government troops in Idlib, north Syria, Saturday, March 10, 2012. U.N. envoy Kofi Annan met with Syrian President Bashar Assad on Saturday in Damascus during a high-profile international mission to mediate an end to the country's yearlong conflict. (Foto:Rodrigo Abd/AP/dapd)
የሶሪያ መንግሥት ጦር በአገሪቱ ሰሜንዊ ክፍለ-ሐገር በኢድሊብ በተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ሲያደርስምስል dapd

ቢይሮን ባላሽከ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ