1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሎኝ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር ተደረመሰ

ዓርብ፣ የካቲት 27 2001

መንገዱ ላይ ቆሜ ልክ ቡና እየጠጣሁ ነበር። ወዲያው መሰነጣጠቅ ጀመረ። የቤተ-መዘክሩ ሠራተኞች በሙሉ ሮጠው ወጡ። በድጋሚ ዞር ብዬ ተመለከትኩ። ከፊት ለፊት ያለው የሕንፃው አካል በሙሉ ሲደረመስ አየሁ። መጀመሪያ የተደረመሰው መሬት ላይ ተከሰከሰከ። ወዲያው ሁላችንም መሮጥ ብቻ ሆነ። ከዚያ ሕንፃው ሙሉ በሙሉ ተደረመሰ።

https://p.dw.com/p/H6vu
የተደረመሰው ሕንፃ ከፊል ገፅታ
የተደረመሰው ሕንፃ ከፊል ገፅታምስል AP
ኮሎኝ ከተማ ውስጥ፥ ጥንታዊ መዛግብትን ያከማቸ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር ማክሰኞ ለት በድንገት መደርመሱ ተዘግቧል። ህንፃው ከተደረመሰ ቀናት ቢያስቆጥርም፤ ፍራስራሹ ውስጥ እንደተቀበሩ የተገመቱት ሁለት ሰዎችን የማዳን ተግባር ግን እስካሁን አልተጀመረም። በተደረመሰው ሕንፃ አካባቢ የሚገኙ ሌሎች ሕንፃዎች እንዳይደረመሱም ተሰግቷል። ቀድሞ አራት መቶ ሚሊዮን ዩሮ ዋስትና የተገባለት ይህ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር በውስጡ ያከማቻቸው ጥንታዊ መዛግብት እንዳይበላሹ ርብርብ እየተደረገ ነው።