1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካሌ ስደተኞች አሳሳቢ ሁኔታ እና የ«ሂውመን ራይትስ ዎች» ዘገባ

ሰኞ፣ ጥር 18 2007

በሰሜን ፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌ የሠፈሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገን ጠያቂ ስደተኞች የኑሮ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ነው ሲል የመብት

https://p.dw.com/p/1EQhO
Flüchtlinge in Calais 28.05.2014
ምስል AFP/Getty Images/Denis Charlet

ተሟጋቹ ድርጅት «ሂውመን ራይትስ ዎች» ወቀሰ። ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው፣ ወደ ብሪታንያ ለመግባት ተስፋ በማድረግ በካሌ የሚገኙት በግምት 2,300 ስደተኞች በፈረንሳይ ፖሊስ የመደብደብ እና ባጠቃላይ የመጉላላት ስቃይ ይደርስባቸዋል። ይህንን የድርጅቱን ወቀሳ የፈረንሳይ መንግሥት ሀሰት ሲል አስተባብሎታል። ስለስደተኞቹ ሁኔታ የፓሪሷ ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ የፓሪስ የ«ሂውመን ራይትስ ዎች» ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ዣን ማሪ ፋርዶን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ