1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኪነ-ጥበብ መድረክ

ሐሙስ፣ የካቲት 27 2006

በኢትዮጵያ ሰዎች በህይወት በነበሩበት ወቅት ማህበረሰቡን የሚጠቅም ነገር ትተዉ ሲያልፉ፤ ስራዉ በቀጣይነት ሲከናወን እና አመርቂ ዉጤት ሲያገኝ የሚታየዉ እጅግ በጥቂት አጋጣሚ ነዉ። የዛሬ 11 ዓመት በኢትዮጵያ የተቋቋመዉ፤ ሚዉዚክ ሜይዴይ የተሰኘዉ ድርጅት፤ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ እየሰራ ያለዉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተጠቃሽ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1BL4e
Prof. Fekade Azeze
ምስል Azeb Tadesse Hahn

መጻህፍትን የማንበብ ባህል እንዲጎለብት፤ እንዲሁም በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ በተለይ የትያትር ትወናና፤ የሙዚቃ ትምህርት ስልጠና በመስጠቱና፤ ጻህፍት በእዉቀት እና በምክንያት ላይ ተመርኩዘዉ ሰፊ የመከራከርያ መድረክ ስለሆናቸዉ ስለ ሚዉዚክ ሜይዴ ኪነ-ጥበባዊ ድርጅት ተግባር መሰናዶ ይዘናል።

የዛሪ ሁለት ሳምንት ግድም የሙዚክ ሜይዴይ መስራች የከያኒ ሽመልስ አራርሶ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበትን ሰባተኛ ዓመት በማስመልከት ሰፊ የስነ- ግጥም የሙዚቃ እና የስነ- ፅሁፍ መድረክ ተዘጋጅቶአል። በርካታ ታዋቂ የስነ-ፅሁፍ ሰዎች የተገኙበት ይህ መድረክ፤ የሚዉዚክ ሜይዴይ፤ የኪነ-ጥበብ መድረክ መስራች ከያኒ ሽመልስ አራርሶን ከመዘከር ባሻገር ስራዉ ህያዉ ሆኖ ከትዉልድ ትዉልድ እንዲሻገር ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎአል። በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ደረሰ ንጋቱ፤ እንደሚሉት መድረኩ፤ የተለያዩ ባለሞያዎች በተለይ በስነፅሁፍ ዙርያ ከፍተኛ ክርክርና መማማር የሚያርጉበት መድረክ ነዉ፤ ለዓመታት የመድረኩ ተሳታፊ እንደሆኑ ገልፀዉልናል።

ድርጅቱ ሲመሰረት በተለይ ወጣቱን ታሳቢ በማድረግ መጀመሩን የነገሩን በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት፤ አቶ ደረሰ ንጋቱ እንደሚሉት መድረኩ በተለይ ትምህርት እና ሥራ የሌለዉን ወጣት ተሳታፊ ለማድረግ አላማ ያደረገ ነዉ። እንደ አቶ ደርሰ ንጋቱ ፤ ሃገሪቱ አላት ከተባሉት ትልልቅ የንባብ መድረኮች አንዱ፤ ሚዉዚክ ሜይዴይ እንደሆንም ተናግረዋል።

ሚዉዚክ ሜይዴይ የተባለዉን የኪነጥበብ መድረክ ለዓመታት፤ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመራ የቆየዉ የሙዚክ ሜይዴይ መስራች ከያኒ ሽመልስ አራርሶ በህይወት በነበረበት ወቅት በስነ-ፅሁፍ መድረክ ዝግጅት ላይ የተሳተፉት ታዋቂዉ ደራሲና ሃያሲ አስፋዉ ፤ ይህ መድረክ ከመገናኛ እና ከመወያያ ባሻገር፤ ታሪክን ለትዉልድ ማዉረሻ መድረክም ጭምር ነዉ። ከሁሉ ከሁሉ ግን ይላሉ ደራሲ አስፋዉ ዳምጤ መድረኩ የቀጠሮ አከባበር ባህልንም ያስተማረ ነዉ።

Asfaw Damte Schriftsteller Music Mayday Ethiopia schlechte Bildqualität
ምስል Azeb Tadesse Hahn

የቁም ነገር መፅሄት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ በዝግጅቱ ላይ ሽመልስ አራርሶ የሰራቸዉን ስራዎች በዘጋቢ መልክ በማቀናበር ማቅረቡም ተነግሮ እል እንደ ጋዜጠኛ ታምራት፤ ፊልሞችና ታሪካቸዉን በመፃፍና አጉልቶ በማዉጣት የኪነ-ጥበብ ሰዎች ስራቸዉን ለተተኪዉ ትዉልድ ማቆየት ሃላፊነት አለብን ሲል ገልፆልናል። የሙዚክ ሜይዴ መስራች የየሽመልስ አራርሶን ሙዚቃ ነበር ያደመጥነዉ። ሚዉዚክ ሜይዴይ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ እያደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ በሌሎች ክፍላተሃገራትም ቢጠናከር ያሉንን የለቱን እንግዶቻችንን እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ