1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከተሞች የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ መስከረም 13 2009

የኢትዮጽያ መንግስት በ36 ቢሊዮን ብር በጀት በከተሞች የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ሊዘረጋ ማቀዱን አስታወቀ።በመርሃ ግብሩ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። መንግሥት እንደሚለው መዲናዋን አዲስ አበባን ጨምሮ በ 11 ከተሞች ተፈጻሚ የሚሆነዉ ይኸዉ እቅድ ከ600 ሺህ በላይ ሰወችን ተጠቃሚ ያደርጋል ።

https://p.dw.com/p/1K7KQ
Karte Äthiopien englisch

[No title]

የከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ አፈጻጸሙ በደንብ ሊታሰብበትና ተጠቃሚዎችም አምነዉበት ወደ ስራ መገባት አለበት ብለዋል። ለከተሞች የታቀደው የምግብ ዋሰትና መርሃ ግብር ከአሁን በፊት ምግብ አጠር በሆኑ የገጠር ቀበሌዎች ነበር የሚተገበረው ። በቀጣይ አሰር አመታት ግን የከተማ ነዋሪውንም ተጠቃሚ የሚያደረግ መሆኑነ የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ በሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታምሩ መከተ ገለፀዋል ።

አንደ አቶ ታምሩ ገለፃ መዲናዋን አዲሰ አበባን ጨመሮ በአሰራ አንድ ከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራሙ ይተገበራል ። በዚህም ወጣቶች ሴቶች አካለጉዳተኞች አረጋዉያን አንዲሁም የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሚካተቱ ድጋፉም በሁለተ መንገድ እንደሚከናወን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ግን አቅዱ ጥሩ ቢሆንም አፈፃፀሙ ላይ ጥንቃቄ ካልተደረገና ተጠቃሚዎቹ አምነውበት ወደ ሰራ ካልገቡ መርሃ ግብር ችግር ይገጥመዋል ይላሉ ።

ተጠቃሚዎችን የመለየት ሥራ በቀጣዩ ታህሳስ ወር ይጀመራል ያሉት አቶ ታምሩ ለአስር አመታት ለሚቀጥለው ለዚህ የሴፍት ኔት መርህ ግብር በአጠቃላይ ሰላሳ ስድሥት ቢሊዮን ብር በጀት መበጀቱንና ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ከተማ መመደቡን ተናግረዋል ። ይህም እየተባባሰ የመጣውን የከተሞች ማህበራዊ ችግር ያቃልላል ብለዋል አቶ ታምሩ።

የመርሃ ግብሩ ማስኬጃ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍና ከመንግስት ወጪ በሚደረግ ገንዘብ እንደሚሸፈንና በመርሃ ግብሩ ከስድስት መቶ ሽህ በላይ ሰዎች እንደሚረዱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዋ ጨምረዉ ገልፅዋል።በኢትዮጵያ ከአሁን በፊት 7.5 ሚሊዮን ህዝብ በሴፍት ኔት የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር እንደታቀፈ፣ 10.5 ሚሊዮን ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደ ሚያስፈልገዉና ከመካከላቸውም 5.8 ሚሊዮን የሚሆነዉ ህዝብ በከፋ የምግብ እጥረት ዉስጥ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ዘገባ ያስረዳል።

ፀሐይ ጫኔ

ኂሩት መለሰ