የኦባማ እና የነታንያሁ ውይይት1 ኅዳር 2002ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 2002የዩናይትስድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ የመካከለኛውን ምስራቅ የሰላም ሂደት ማፋጠን በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትናንት ማምሻውን መክረዋል ።https://p.dw.com/p/KTMtኔታንያሁ ከኦባማ ጋር ከተገናኙ በህዋላምስል APማስታወቂያዋይት ሀውስ ውስጥ በጋራ ጉዳዮች ላይ በዝግ የመከሩት ሁለቱ መሪዎች አንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ከፈጀው ውይይታቸው በኃላ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሰጡም ። ነታንያሁ ከፕሬዝዳንት ኦባማ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ባሰሙት ንግግር የእስራኤል ፍልስጤም የሰላም ጥረት ከዳር ለማድረስ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀው ነበር ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል ። አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ