1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ ና የኔታንያሁ ውይይት

ረቡዕ፣ የካቲት 28 2004

ከዩናይትድ ስቴስትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ትናንት ዋሽንግተን ውስጥ የተነጋገሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃገራቸው እስካሁን የኢራን የኒዩክልየር ተቋማትን የማጥቃት ውሳኔ ላይ አለመድረሷን አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/14G4y
ኦባማና ነታንያሁምስል dapd

ከዩናይትድ ስቴስትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ትናንት ዋሽንግተን ውስጥ የተነጋገሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚንኔታንያሁ  ሃገራቸው እስካሁን የኢራን የኒዩክልየር ተቋማትን የማጥቃት ውሳኔ ላይ አለመድረሷን አስታወቁ ። ሆኖም ነታንያሁ እስራኤል ፣ ራስዋን  በወታደራዊ እርምጃ ከጥቃት የመከላከል ውሳኔ ላይ የመድረስ መብትዋን  ለወደፊቱ  እንደያዘችው ተናግረዋል ። ኦባማ በበኩላቸው በኢራን ላይ ማዕቀቦችን ከመጣል ይልቅ ለዲፕሎማሲው ጥረት ይበልጥ ጊዜ እንዲስጥ አሳስበዋል ።እስራኤል ግን በኢራን የኒዩክልየር መርሃ ግብር  ሰበብ የተነሳውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ መፈታት መቻሉን ትጠራጠራለች ። ክላውስ ካስታን ያቀረበውን ዘገባ  ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለችዩናይትድ  ስቴትስም ሆነች እስራኤል የቴህራን መሪዎች የአቶም ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳይሆኑ መግታት ነው ፍላጎታቸው ። ይህ ግን እንደፈለጉት ሊሰምር አልቻልም ። ቢሆንም  በትናንቱ መግለጫቸው ይህን ብዙም አጉልተው አላወጡትም ። ከዚያ ይልቅ ግንኙነታቸው በጥብቅ መሠረት ላይ የቆመ ወዳጅንታቸውም የጠነከረ መሆኑ ላይ ነበር ያተኮሩት  ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ  ሃገራቸው ለእስራኤል ደህንነት ያላትን ቁርጥኝነት  ዳግም አረጋግጠዋል ።

Netanjahu und Obama
ምስል dapd

« የእሰራኤልን ደህንነት ለማስከበር ያለን ቁርጠኝነት ፍፁም የጠጠረ ነው ።

ነተንያሁ ድግሞ በምላሹ አሜሪካንና እስራኤል እንድም ሁለትም መሆናቸውን መሰከሩ ።

«እኛ እናንተ ነን ። እናንተ ደግሞ እኛ ናችሁ ። አንድ ላይ ነን ።

የዩናይትድ ስቴስትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ  ትናንት ዋሽንግተን ውስጥ ያካሄዱት ውይይት ልዪ ትኩረት በኢራን የኒዩክልየር መርሃ ግብር ላይ እስራኤል ያደርባት ስጋት ነበር ። ኢራን የኒዩክልይር ጦር መሣሪያዎች ባለቤት ለመሆን  አላት የሚባለው ጉጉትና የኢራን መሪዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት እስራኤል ከዓለም ካርታ መጥፋት አለበት ሲሉ መዛታቸው ፣ኢራን እስራኤል ለህልውናዋ እጅግ አስጊ አደርጋ የምትቆጥራት ሃገር ናት ። ነተንያሁ ትናንት እንዳስታወቁት እስራኤል በህልውናዋ በመጣ ጉዳይ ላይ  አትደራደርም  ። ራስዋን የመከላከል እርምጅዎችንም ከመወሰድ ወደ ኋላ አትልም   

« የእስራኤልን ደህነንት በሚመለከት ፣ እስራኤል የራስዋን እርምጃዎች የመወሰድ ሉዓላዊ መበት እላት »

Treffen Barack Obama und Benjamin Netanjahu in Washington
ምስል dapd

ምንም እንኳን እስካሁን አንድም የእስራኤል መሪ ኢራንን ለማጥቃት በይፋ ማስጠንቀቂያ ባይናገርም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ይህን መሰሉ እርምጃ እንዲወስድ ፈቃድ የመገኝቱ ጭምጭምታ ሲሰማ ነበር የከረመው  ። ይሁንን ክኦባማ ና ክንትንያሁ ንግግር በኋላ እስራኤል አሰቀድማ ይዛላቸ በተባለው እቅዷ መሠረት በኢራን የኒዩክልየር ተቋማት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ አለመውሰዷ በግልጽ አልታወቀም ። ባራክ ኦባማ ግን  ወታደራዊ እርምጃ መወሰዱን እስካሁን ድረስ አይቀበሉም ። ክዚያ ይልቅ ሌሎች አማራጮች ይሞከሩ ነው የሚሉት   ። ባለፈው እሁድ በዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኢል ድጋፍ በማሰባሰብ በሚታወቀው በእንግሊዘኛው ምህፃር AIPAC በተባለው ድርጅት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ኢራን የኒዩክልየር ቦምብ ባለቤት እንዳትሆን ሃገራቸው ያሉትን አማራጮች ሁሉ ክፍት አንደምታደርግ  አሰታውቀው ነበር ። ኦባማ በኢራን ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በመጪዎቹ ወራቶች የሚያመጡትን ወጤት እንጠብቅ ነው የሚሉት ። በምንም ዓይነት መንገድ ሃገራቸው ሌላ ጦርነት ወሰጥ እንድትገባ እንደማይፈልጉ ነው ያሳውቁት ። ትናንት ከነታንያሁ ጋር ከተወያዩ በኋላም ከቴህራን ጋር ስላለው  ውዝግብ  ሲያውሱ ዲፕሎማሲ የሚልውን ቃል ሶስት ጊዜ አንስተዋል ።

« አሁንም ለጉዳዩ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ  የሚያስገኝ ተስፋ አለ ። ሆኖም በሰተመጨረሻ የኢራንን አገዛዝም  በዚህ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ እስካሁን ያላደረገው ውሳኔ ላይ መድረሰ  አለበት ።  »

ለኦባማ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት ኦባማ የእስራኤሉ እንግዳቸው በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃዎች ከመውሰድ እንዲቆጠቡ አበክረው መክረዋል ። ኦባማ እስራኤል በአሁኑ ሰዓት ኢራንን እንዳትመታ የጠየቁት በምትኩ ለእስራኤል ምን ለማድረግ አስበው ይሆን የሚሉ ወገኖች አሉ ታዛቢዎች እንደሚሉትእስራኤል የአሜሪካንን ጥያቄ የምትቀበል ከሆነ በምትኩ ደግሞ ከዋሽንግተን የሆነ ነገር ትቀበላለች ። ምናልባት ዲፕሎማሲውም ማዕቀቡም አልሰራ ብሎ ወደ ወታደራዊ አርምጃ የሚገባ ከሆነ እርምጃ የምትወስደው እስራኤል ብቻ ሳትሆን አሜሪካ ጭምር ልትሆን ትችላለች የሚል ማካካሻ ለእስራኤል ቃል ሳይገባላት አይቀርም  ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ