1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮምያ ተማሪዎች ተቃውሞና የምሁራን አስተያየት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2008

በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና በምኒያፖሊስ ምኒሶታ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆችም ለኦሮሞ ተማሪዎች ያላቸውን አጋርነት በሰላማዊ ሰልፍ፣በሻማ ማብራትና በተለያዩ የውይይት መድረኮች በመግለፅ ላይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/1HSSn
Oromo Proteste in Äthiopien
ምስል Oromia Media Network


በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ዘንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። Oromoprotest በተባለው የተቃውሞ ዘመቻ በፌስቡክ ከ98ሺ፣በትዊተር ደግሞ ከ57ሺ በላይ ሰዎች መረጃዎች ተለዋውጠዋል። በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና በምኒያፖሊስ ምኒሶታ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆችም ለኦሮሞ ተማሪዎች ያላቸውን አጋርነት በሰላማዊ ሰልፍ፣በሻማ ማብራትና በተለያዩ የውይይት መድረኮች በመግለፅ ላይ ናቸው። ያገረሸው የኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃውሞ የአዲስ አበባና የኦሮምያ የተቀናጀ እቅድ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ገንፍሎ የወጣበትም ነው ሲሉዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኦሮሞ ምሁራን ይገልጻሉ።የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ በጉዳዩ ላይ ዩናይትድስቴትስ የሚገኙ ሁለት የኦሮሞ ምሁራንን አነጋግሮ ታከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ