1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች ግጭት የመጀመሪያ የምርመራ ውጤት  

ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 2010

በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች በሚያዋስኗቸው ወረዳዎች የተቀሰቀሰው ግጭት  ብዙ መፈናቀል ማስከተሉን  የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2m6Pj
Äthiopien Negeri Lencho
ምስል DW/G. Tedla

የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልሎች ግጭት ሰለባዎች

የመፈናቀል እጣ የገጠማቸውን ዜጎች ለመርዳት በክልል እና በፌዴራል በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚንስትሩ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በግጭቱ  በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ለደረሰው ጥፋት እና ጉዳት ተጠያቂ የሆኑት የፀጥታ ኃይላት እንደሚታወቁ ዶክተር ነገሪ ተናግረው፣ በነዚህ ወገኖች ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ጉዳዩን የማጣራት ስራ እንዳበቃ ወደፊት እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ