1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦሮሚያ መስተዳድር አዳዲስ ሹማምንት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 10 2010

ከመስተዳድሩ ምክትል ፕሬዝደንት ጀምሮ እስከ ከተማ ከንቲቦች በሚደርሱ የሥልጣን ደረጃዎች እስካሁን በመስተዳድሩም ሆነ በፓርቲዉ ዉስጥ ብዙም የማይታወቁ ፖለቲከኞችን ተሾመዋል።መግለጫዉ እንደሚለዉ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች የማስፈፀም ብቃት ያላቸዉ ፖለቲከኞች ናቸዉ

https://p.dw.com/p/2wHQj
Lema Megerssa
ምስል DW/S. Teshome

(Q&A) Mit Halrluya-Oromia reshuffel - MP3-Stereo

የኦሮሚያ መስተዳድር ገዢ ፓርቲ የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ ባለስልጣናት ሹም ሽር አደረገ።መስተዳድሩ ዛሬ ባሰራጨዉ መግለጫ ከመስተዳድሩ ምክትል ፕሬዝደንት ጀምሮ እስከ ከተማ ከንቲቦች በሚደርሱ የሥልጣን ደረጃዎች እስካሁን በመስተዳድሩም ሆነ በፓርቲዉ ዉስጥ ብዙም የማይታወቁ ፖለቲከኞችን ተሾመዋል።መግለጫዉ እንደሚለዉ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች የማስፈፀም ብቃት ያላቸዉ ፖለቲከኞች ናቸዉ።የፖለቲካ ተንታኝ ሐሌሉያ ሉሌ እንደሚሉት ደግሞ ባለፈዉ አንድ ዓመት ተኩል  ከአራቱ የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች «ያፈነገጠ» ዓይነት አቋም ያንፀባርቅ የነበረዉ ኦሕዴድ አሁን  ለዉጥ ያደረገዉ ለወደፊቱ ይበልጥ ለመጠናከር አስቦ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አቶ ሐሌሉያ ሉሌን አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ