1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ውይይት በኢጣልያ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2001

አዲሱ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን በኢጣልያ ከጠቅላይ ሚንስትር ሲልቭዮ ቤርሉስኮኒ እና ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንኮ ፍራቲኒ ጋር ተገናኝተው ስለ እስራኤል የውጭ ፖሊሲ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

https://p.dw.com/p/Hk9z
ምስል AP

በዚሁ ስልጣናቸው ዛሬ ወደ ፈረንሳይ፡ በሚቀጥሉት ቀናት ደግሞ ወደ ቼክ ሬፑብሊክ እና ወደ ጀርመን የሚያመሩት ሊበርማን የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የፊታችን ዓርብ በእስራኤል የሚጀምሩት ጉብኝታቸው በእስራኤልና በለዘብተኛ ዐረብ ሀገሮች፡ እንዲሁም፡ በክርስትና እና በአይሁድ እምነት መካከል ለሚደረገው ውይይት ትልቅ ትርጓሜ እንዳለው አስታውቀዋል።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ/አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሐመድ