1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2008

የዓለም የጤና ድርጅት በአዳጊ ሃገራት የሚገኙ 225 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች እርግዝና እንዳይከሰት ለማድረግ ወይም ለማዘግየት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የወሊድ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1H3Zz
Yasmin Antibabypille
ምስል Bayer Schering Pharma AG / Matthias Lindner

የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች

ለዚህም በዋናነት፤ አማራጭ ማጣት፤ መድኃኒቶቹን እንደልብ አለማግኘት፤ በባህል ወይም ሃይማኖታዊ ምክንያቶች፤ ደረጃዉን የጠበቀ አገልግሎት አለማግኘት፤ ተጠቃሚዎቹም ሆኑ አቅራቢዎቹ ባላቸዉ የተዛባ አመለካከትና የመሳሰሉትን በምክንያትነት ይዘረዝራል። በበርካታ የዓለም ክፍሎች የወሊድ መከላከያ መድኃኒቶችን መጠቀም እየጨመረ መሄዱን የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይም በእስያ እና ላቲን አሜሪካ ከ61 በመቶ እስከ 66 በመቶ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር ከፍ ማለቱ ተመዝግቧል። መረጃዉ እንደሚያሳየዉ በተቃራኒዉ ከሰሀራ በስተደቡብ በሚገኙ ሃገራት ይህን መድኃኒት የመጠቀሙ አዝማሚያ ዝቅተኛ ነዉ። ይህ እንግዲህ ሴቶችን በሚመለከት ነዉ። የእርግዝና መከላከያ ስልቶችን የሚጠቀሙ ወንዶች ቁጥር እንደየዓለም የጤና ድርጅት ከሴቶቹ ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ነዉ። ለወንዶቹ ያለዉ የመከላከያ መንገድም አማራጩ ዉሱን ነዉ። የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶችን መጠቀም ለባለትዳሮች የልጆችን ቁጥር ከመመጠኑ ሌላ ፅንስ ማስወረድን ለማስቀረት ዋነኛ መፍትሄ እንደሆነ የዓለም የጤና ድርጅት ያስረዳል። በሌላ በኩል መድኃኒቶቹ ከሚሰጡት ተፈላጊ ጥቅም ባሻገር እንደየሰዉ የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶችም እንዳሏቸዉ የአሜሪካን የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር በድረገጹ ይዘረዝራል። ከታወቁና የተለመዱ ከተባሉት መካከል የራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ እና ክብደት መጨመርን ይጠቀሳሉ። ከሰሞኑ በጀመርን የመገናኛ ብዙሃን ከተደመጡት ችግሮች ደግሞ የደም መርጋት እና በዚህ መዘዝ የሚከተል የልብ ሕመምም ማስከተላቸዉ በዋነኛነት የመድኃኒቱ ተጠቃሚዎች እና የህክምና ባለሙያዎችን ትኩረት ስበዋል። ሽተርን ቴፋዉ በተሰኘዉ አንድ የጀርመን የቴሌቪዝን ጣቢያ ሳምንታዊ ዝግጅት ላይ ጉዳዩ ለዉይይት እንዲቀርብ ምክንያት የሆነዉ አዳዲስ ገበያ ላይ የዋሉ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶችን በመዋጥ ምክንያት የተተለያዩ ሴቶች ደረሰብን ያሉት የጤና ችግር ነዉ። ችግሩ እንዳለ በማመልከትም ያልታቀደ እርግዝናን ለመከላከል ሲባል በተለይ ወጣቶችና ትዳር ያልመሠረቱ ሴት ልጆች ያገኙትን መድኃኒት ከመዉሰድ እንዲታቀቡ ነዉ ባለሙያዎች የመከሩት።

Die erste Antibabypille
የመጀመሪያዉ የእርግዝና መከላከያ እንክብልምስል AP
Symbolbild Frau Einnahme Tablette
ምስል Fotolia/Doruk Sikman

ግሪክ ዉስጥ ሲሮስ በተባለችዉ የደሴት ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ የሚገኘዉ ሲሮስ ሆስፒታል የጽንስና ማህጸን ሃኪምና የህክምና ክፍሉ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር መኮንን ዱባለ ነጋሽ ከእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶች ችግር ያስከተሉ መኖራቸዉን በመጠቆም ለችግር ሊሆን ይችላል ያሉትን ምክንያት እንዲህ ያስረዳሉ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ