1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርዳታ እህል እንደፖለቲካ መሳሪያ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2002

«የእርዳታ እህልን በድርቅ ለተጎዱት ለሁሉም ዜጎች እኩል እያከፋፈልኩ ነዉ።» የመንግስት አካል ምላሽ፤

https://p.dw.com/p/LD0f
ምስል Helge Bendl

የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሰጠዉን ሰብዓዊ ርዳታም ሆነ የዕለት ደራሽ ምግብ የሚያድለዉ በፖለቲካ ወገንተኝነት ነዉ፤ ርዳታዉን ለማግኘት የገዢዉ ፓርቲ አባል ወይም ደጋፊ መሆን በመስፈርትነት ይጠቀማልና ሌሎችም ተያያዥ ክሶች ከአንዳንድ ለጋሽ ድርጅቶችና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽንን በበላይነት የሚያስተዳድረዉ የኢትዮጵያ ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ክሱ በስማ በለዉ የሚቀርብ፤ በቂ ማስረጃ ሊቀርብበት የማይችል፤ የፖለቲካ ፍላጎትና ድብቅ ዓላማን ለማስፈፀም የታለመ መሠረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል።

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ