1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሥልምና ሃይማኖት ትምሕርት በኖርድ ራይን ቬስትፋለን

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 29 2004

በምዕራብ ጀርመኑ የኖርድ ራይን ቬስትፋለን ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ከ2 ሳምንት አጋማሽ በፊት በተጀመረው በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት ለመሰጠት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል ። ለዚሁ አላማ የሚውል የትምህርት መርጃ መፀሐፍም ተዘጋጅቷል ።

https://p.dw.com/p/163Y9
Miteinander auf dem Weg (Buchcover); Illustratorin: Liliane Oser, Hamburg; Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart***Das Bild darf nur im Rahmen einer Buchbesprechung benutzt werden

በምዕራብ ጀርመኑ የኖርድ ራይን ቬስትፋለን ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ከ2 ሳምንት አጋማሽ በፊት በተጀመረው በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት ለመሰጠት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል ። ለዚሁ አላማ የሚውል የትምህርት መርጃ መፀሐፍም ተዘጋጅቷል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ሙስሊም ይኖርባታል በሚባለው በጀርመን ከ1999 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለሙከራ ተብሎ የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት በአንዳንድ የጀርመን ትምህርት ቤቶች ይሰጥ ነበር ። ከዛሬ 2 ሳምንት ጀምሮ ግን በኖርድ ራይን ቬስትፋለን ለመጀመሪያ ጊዜ የእስልምና ትምሕርት በመደበኛ ትምህርትነት ለ1 ኛ ደረጃ ተማሪዎች  ለመሰጠት እንቅስቃሴዎች ተጀምሯል ። በዚሁ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች የእስልምናን ባህላዊ እሴቶችና ደንቦችን ይማራሉ ። ለዚሁ ዓላማም የትምህርት መርጃ መፀሐፍ ተዘጋጅቷል ። መፀሐፉ ወደፊት እስከ 2 ተኛ ደረጃ ድረስ እንዲዘልቅ ይደረጋል ተብሎ ለሚታሰበው ለዚህ ትምህርት መሠረት ይጥላል ተብሉ ይታመናል ። የእስልምና ጉዳዮች አጥኚ ሚኻኤል ኪፈር እንዳሉት « በአንድነት ጉዞ » የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ የትምሕርት መርጃ መፀሀፍ በስእል የተደገፈ በመሆኑ ተማሪዎች በቀላሉ ሊረዱት ይችላሉ

Islambuch: Interreligiöse Lebenswirklichkeit; Die Protagonisten leben in einer Gesellschaft, in der Christentum, Judentum und der Islam gleichberechtigt Raum finden. Islamwissenschaftler Michael Kiefer hat den interreligiösen Teil des Buches als besonders gelungen hervorgehoben; Copyright: Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser
ምስል Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser

« እርግጥ ነው ይሄ ትምህርት ለ1 ና 2ተኛ ክፍል ተማሪዎች የሚጠቅም ነው ። በዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት በተለይ ለ 1 ኛ ክፍል ተማሪዎች ያን ያህልም ማንበብ ለማይችሉ በስእል እርዳታ ማቅረቡ የተለየ ትርጉም እንዳለው ነው ። » 

በተለይም ለ 1 ኛ ና 2 ተኛ ክፍል ተማሪዎች በተዘጋጀው የትምሕርት መርጃ መፀሐፍ ውስጥ መሰረታቸው የውጭ የሆነ ሳራና ቢላል የተባሉ ልጆች ታሪክ ተካቷል ። ሁለቱ ልጆች ህፃናት ሊረዱ በሚችሉበት አቅም መፀሀፉ የሳራ ወላጆች ከሳውዲ አረቢያ የቢላል ደግሞ ከ ቱርክ ወደ ጀርመን የመጡ መሆናቸውን በመተረክ ነው የሚጀምረው ። በዚህ መፀሃፍ ሌሎች ሃይማኖቶችም ይጠቀሳሉ ። የእስልምና ሃይማኖት ጉዳዮች አጥኚው ሚኻኤል ኪፈር ከመፀሐፉ ውስጥ አንዳንዱን ክፍል መተቸታቸው አልቀረም 

«የወደድኩት ነገር ቢኖር ስለ ሃይማኖቶች መወራረስ የሚያወሳውን ክፍል ነው ። ይህ እጹብ ድንቅ ሆኖ ነው የተዘጋጀው ። ምክንያቱም መፀሐፉ ስለ ይሁዲ እምነትና ስለ ክርስትና ምንነት ያስተምራል ። ያልወደድኩት በታሪኩ ላይ የጠቀሱት 2ቱ ልጆች የሳራና የቢላል  ወላጆች ወደ ጀርመን ተሰደው የገቡ መሆናቸው ነው ። እንደኔ ግምት ጥሩ የሚሆን የነበረው እስልምና ያን ያህል የውጭ ዜጎች ሃይማኖት የሆነ አስመስሎ ማቅረቡን ነው ። መዘንጋት የሌለብን ቱርኮች ወደ ጀርመን ለሥራ እንዲገቡ የተደረገበትን ስምምነት 50 ኛ አመት ባለፉት አመታት አክብረናል ። ያ ማለት ከዚያን ጊዜ አንስቶ በጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች እኛ እዚህ የምንኖር 4 ተኛ ትውልድ ላይ የምንገኝ መሆናችን ነው ። »

Islambuch: Interreligiöse Lebenswirklichkeit; Die Protagonisten leben in einer Gesellschaft, in der Christentum, Judentum und der Islam gleichberechtigt Raum finden. Islamwissenschaftler Michael Kiefer hat den interreligiösen Teil des Buches als besonders gelungen hervorgehoben; Copyright: Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser
ምስል Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser

መሐመድ ኮርሺድ ከመፀሃፉ 6 ደራሲዎች አንዱ ናቸው ። እርሳቸውና ሌሎች ደራሲዎች ፣ የምሁራንን የሙስሊሙን ማህበረሰብ እንዲሁም የወላጆችና ተማሪዎችን ፍላጎት ለሟሟላት የተቻላቸውን ሙከራ አድርገዋል ።  

 « ማድረግ የፈለግነው ለሁሉም የሚስማማ የእስልምና ትምሕርት መፀሐፍ ማዘጋጀት ነበር ። የሙስሊሙ ማህበረሰብም  በጀርመን ሃገር የእስልምና ትውፊትና ሃይማኖቱ እ ንዲሁም መለያውም ሆነ መታወቂያው እንዲጠበቅ ነው ፍላጎቱ ። ይህ አንዱ ተግዳሮት ነበር ። እናም ዘመናዊውና ባህላዊው ሚዛኑን ጠብቆ እንዲቀርብ ለማድረግ ሞክረናል ። »

በመፀሐፉ ውስጥ የተካተቱት የሳራና የቢላል እናቶች ቤት ውስጥ አይከናነቡም መፀሃፉ ውስጥ ያሉት ገፀ ባህርያት በውጭ አንዳንዴ ራሳቸውን ሸፍነው ይታያሉ አንዳንዴም አይሸፍኑም ። ይህን ጉዳይ በትምህርት መርጃው መፀሐፍ ውስጥ በጥንቃቄ ለማካተት መሞከሩን ነው ኮርሺድ የሚናገሩት ።

« ለምሳሌ ራስ መከናነብን በተመለከት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመፀሃፉ ውስጥ አንዲት ሙስሊም አስተማሪ ራስዋን እንድትከናነብ ይጠብቅ ይሆናል ። በጀርመን መርህ ግን አስተማሪዎች መከናነብ አይፈቀድላቸውም ። እናም ይሄንን እንዴት መወጣት ይቻላል ? ብለን በመፍትሄነት በስእሉ ላይ  አስተማሪው ወንድ እንዲሆን አድርገናል ። »

Islambuch: Szene aus dem Islamunterricht; Herausgeber und Autor Mouhanad Khorchide hat sich bei Unterrichtsszenen wie dieser für eine männliche Lehrkraft entschieden. Ein Kompromiss. Denn Vertreter von Islamverbänden favorisieren vielfach bedeckte Frauen, was jedoch wegen des Kopftuchverbots an Schulen in Deutschland nicht möglich ist (Illustration auf S. 9); Copyright: Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser
ምስል Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser

ይም ሆኖ መፀሐፉ በተለይ አንዳንድ እውነታዎችን እንዳሉ ባለማቅረብ ወይም ትክክለኛ ትርጉሞችን ባለመስጠት ከተለያየ አቅጣጫ መተቸቱ አልቀረም ። ለምሳሌ መፀሃፉ   የጀርመንኛውን ጎት ወይም እግዚአብሄር የሚለውን ቃል  ከመጠቀም ይልቅ የአረብኛውን ቃል አላህን መውሰዱ በአንዳንድ ወገኖች አስተችቶታል ። ከተችዎቹ መካከል የሃይማኖት ትምህርት መምህርና አሳታሚው ላምያ ካዶር አንዱ ናቸው ።

« እንደሚመስለኝ እንደ የሃይማኖት ትምህርት አስተማሪ ና አሳታሚ አንድ መፀሐፍ ሲያቀርብ  ጠቅላላውን ይዘት ሳያዛንፍ ማቅረብ ይኖርበታል ። የእስልምናውን ትምህርት ለሚከታተሉት ሰዎችም ሃላፊነት አለበት ። እነዚህ ተማሪዎች አላህና እግዚዘብሔር አንድ አይደሉም የሙስሊሞቹ ፈጣሪ አላህ የሌሎቹ ደግሞ እግዚአብሄር የሚሉ ከሆነ ለዚህ ሃላፊነት መውሰዱ ይከብደኛል »  

Islambuch: Szene aus dem Islamunterricht; Herausgeber und Autor Mouhanad Khorchide hat sich bei Unterrichtsszenen wie dieser für eine männliche Lehrkraft entschieden. Ein Kompromiss. Denn Vertreter von Islamverbänden favorisieren vielfach bedeckte Frauen, was jedoch wegen des Kopftuchverbots an Schulen in Deutschland nicht möglich ist (Illustration auf S. 9); Copyright: Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser
ምስል Ernst Klett Verlag GmbH, Stuttgart/Liliane Oser

ሙንሰትር የሚገኘው የእስልምና ትምሕርት ማዕከል ሃላፊ ሙሃናድ ኮርሺዴ ከአሁን በኋላም ከዚህ መፀሐፍ ጋራ ተያይዞ ከባህላዊውና ከዘመናዊው ወገን እንዲሁም ከመንግስትና ከሃይማኖት ተቋማት በኩል የሚነሱ አወዛጋቢ ጉዳዮችን ማስተናገዳቸውን ይቀጥላሉ ። ለ1 ኛ ና  2ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከተዘጋጀው በአንድነት ጉዞ ከተባለው መፀሐፍ በተጨማሪ ሌሎች አጋዥ የትምህርት መርጃዎችን የማዘጋጀት እቅድ አለ ። እስልምናና የሙስሊሞች ጉዳይ በየጊዜው የመነጋገሪያ ርዕስ በሆኑባት በጀርመን የእስልምና ሃይማኖት ትምሕርት ለመስጠት የተጀመሩት እንቅስቃሴዎች አበረታች ተደርገው ነው የሚታዩት ። በኖርድ ራይን ቬስትፋለን ፌደራዊ ክፍለ ሃገር ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መካከል የአንዳንዶቹን አስተያየት ጠይቄ ነበር ። አቶ መኪ ረዲ የኮሎኝ ነዋሪ ናቸው ። የመጀመሪያዋ ሴት ልጃቸው በቅርቡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ጀምራለች ። በሚኖሩበት ፌደራዊ ክፍለ ሃገር የእስልምና ሃያማኖት ትምህርት ለመስጠት የተጀመረው እንቅስቃሴ አስደስቷቸዋል  ።   

አቶ አንዋር ሚፍታህ ጀርመን ሲኖሩ 21 አመታት ተቆጥረዋል ። በኮሎኝ ከተማ ሲኖሩ ደግሞ 12 አመት ሆኗቸዋል ። የ 4 አመት ልጅ አላቸው ። ከ አንድ ወይም ከ2 አመት በኋላ ትምህርት ቤት ይገባል ። የእስልምና ሃይማኖት መሰጠቱ የሚያስገኘውን ጥቅም ሰፋ አድርገው ነው የተመለከቱት ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ