1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤፌኮ አመራር አባላት የፍርድ ቤት ዉሎ፤

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 19 2010

የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና አቃቤ-ሕግ አዲስ ያቀረበባቸዉን የሲዲ ማስረጃ ተቃወሙ። ጠበቃቸዉ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ዋናው የተቃዉሞው መነሻ የማስረጃዉ አቀራረብ ስርዓቱን የተከተለ ባለመሆኑ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2q3gI
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

የፍርድ ቤት ዉሎ

 ከዚህም ሌላ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እጃቸዉ የሚታሠርበት ካቴና እንደቀረ፤ የሚጎበኟቸዉ ጠበቆም ሆነ የቤተሰብ ጉዳይም በችሎቱ እንደታየም አመልክተዋል። በተያያዘ የፍርድ ቤት ውሎ የዚሁ ፓርቲ አመራር የሆኑት የነአቶ በቀለ ገርባም ጉዳይ ዛሬ የታየ ሲሆን፤ ለምስክርነት የጠሯቸው የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተለዋጭ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ እንዲሰጣቸዉ መጠየቃቸው ተሰምቷል። አቶ ወንድሙ እንዲያብራሩልኝ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ጠይቄያቸዋለሁ። 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ