1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ስደተኞች UNHCR እና ኢጣልያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2001

የኢጣልያ መንግስት ከዛሬ አስራ አምስት ቀን በፊት ወደ ኢጣልያዋ የወደብ ከተማ ላምፔዲዛ በተጠጉ ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎች ላይ በወሰደው ዕርምጃ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ተወቅሷል ።

https://p.dw.com/p/IqBG
ምስል AP

በወቅቱ የስደተኞቹን መርከብ ያስቆመው የኢጣልያ ባህር ኃይል ስደተኞቹን በኃይል ወደ ሊቢያ መርከብ አዛውሮ ወደ ሊቢያ ሲያግዝ ፣ ከመካከላቸው የተወሰኑት መቁሰላቸውና በኢጣልያ ቆይታቸውም ምግብ አለማግኘታቸው ተዘግቧል ። በተጨማሪም እነዚሁ ሰዎች የግል ንብረቶቻቸው እና ሰነዶቻቸውም እንደተወሰደባቸው ተነግረዋል ። እነዚህን መረጃዎች ከስደተኞቹ ያገኘው UNHCR ከኢጣልያ መንግስት ማብራሪያ የሚጠይቅ ደብዳቤ ልኳል ። ወቀሳው የቀረበበት የኢጣልያ መንግስት ክሱን በሙሉ ሀሰት ሲል ለደረሰበት ስም ማጥፋት ይቅርታ ልጠየቅ ይገባል ብሏል ። ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ከሮም

ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ፣ ሂሩት መለሰ /ሸዋዬ ለገሠ