1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

    የኤርትራ ማዕድን አዉጪ ኩባንያ ክስ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2010

ኤርትራ ዉስጥ ማዕድን የሚያወጣዉ ነብሱን የተባለ የካናዳ የማዕድን ኩባንያ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር አስገድዶ በዝብዞናል የሚሉ ስድት ኤርትራዉያን ኩባንያዉን ከሰዋል

https://p.dw.com/p/2oP78
Eritrea Bisha Mine bei Asmara
ምስል Reuters/T. Mukoya

mmt (Beri.Toronto) Eritrea Mining abuse-Canadian court - MP3-Stereo

ቢሻ በተባለዉ የኤርትራ ማዕድን ማዉጪያ ሥፍራ ተፈፅሟል የተባለዉን በደል የካናዳ ፍርድ ቤት እንዲመረምር ተወሰነ።ኤርትራ ዉስጥ ማዕድን የሚያወጣዉ ነብሱን የተባለ የካናዳ የማዕድን ኩባንያ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር አስገድዶ በዝብዞናል የሚሉ ስድት ኤርትራዉያን ኩባንያዉን ከሰዋል።ኩባንያዉ ተፈፀመ የተባለዉ በደል ተፈፅሞ ከሆነ የተፈፀመዉ ኤርትራ ዉስጥ በመሆኑ ክሱም መመስረት ያለበት ኤርትራ ዉስጥ ብሎ ሲከራከር ነበር።ይሁንና የካናዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ በካናዳ ፍርድ ቤት እንዲታይ በይኗል።የቶሮንቶዉ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ታሪኩን ተከታትሎታል።

አክመል ነጋሽ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ