1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራና የጅቡቲ ዉዝግብና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

ሐሙስ፣ መጋቢት 24 2001

ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደሚሉት ግን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ መንግሥት ላይ አስገዳጅ ዉሳኔ ማሳለፍ አለበት

https://p.dw.com/p/HOeg
ዋና ፀሐፊ ፓንምስል AP

ኤርትራ በሐይል ይዛዋለች ከሚባለዉ የጅቡቲ ግዛት ለቅቃ-አለመዉጣትዋን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አስታወቁ።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ከትናንት በስቲያ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት ኤርትራ የጅቡቲን ግዛት እንድትለቅ ምክር ቤቱ ባለፈዉ ጥር ያሳለፈዉን ዉሳኔ አላከበረችም።የኤርትራ የያዝኩትም የተያዘብኝም ግዛት የለም ባይ ናት።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደሚሉት ግን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ መንግሥት ላይ አስገዳጅ ዉሳኔ ማሳለፍ አለበት።አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።