1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤሌክትሮኒክ መረጃ እና የመምህራን እጥረት በአፍሪቃ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 19 1999

በኢኮኖሚ በበለጸጉት አገራት የሚኖሩ ህጻናት፣ በትምህርት ገበታ ላይ መፈጸም የሚገባቸዉን እንደ ማንበብ መጻፍ እና የሂሳብ ስሌት ትምህርት ያለ ፍላጎት ሲሰሩ ይታያል

https://p.dw.com/p/E0gy
በሩዋንዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
በሩዋንዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤትምስል DW/Christine Harjes

ባንጻሩ በአፍሪቃ ያሉ ህጻናት ይህን መሰሉን እድል አጥተዉ መማር የሚችሉበትን ዘዴ ሲያፈላልጉ ይታያል። በአፍሪቃ 50 ሚሊዮን ህጻናት ትምህርት ቤት ስለሌለ በትምህርት ገበታ መቅረብ አልቻሉም። በአፍሪቃ እና በበለጸጉት አገራት መካከል ያለዉ ይህን የትምህርት ልዩነት እና የትምህርት ፍላጎት በኢንተርኔት ድጋፍ መቀነስ ይቻላል?