1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣልያ ፕሬዚደንት የድል ሐውልት ጉብኝት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2008

የኢጣልያ ፕሬዚደንት ሴርጂዮ ማታሬላ ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ በጀመሩት የአምስት ቀን ጉብኝታቸው ዛሬ በአዲስ አበባ በአራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።

https://p.dw.com/p/1IDP0
ፕሬዚደንት ሴርጂዮ ማታሬላ ከኢትዮጵያዊ አርበኛ ጋር
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

ከፋሺስት ኢጣልያ ጋር ከተፋለሙት መካከል በሕይወት ያሉት አርበኞች በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ በመገኘት ለኢጣልያዊው ርዕሰ ብሔር በሰልፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢጣልያዊው ፕሬዚደንትም የእያንዳንዱን አርበኛ እጅ በመጨበጥ ሰላምታ ሰጥተዋቸዋል። አንድ የኢጣልያ ፕሬዚደንት ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ማታሬላ ሁለተኛው ናቸው። እንደሚታወሰው፣ የቀድሞው ፕሬዚደንት ኦስካር ልዊጂ ስካልፋሮ እጎአ ህዳር ፣ 1997 ዓም ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ