1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣልያ ፕሬዚደንት በአፍሪቃ ህብረት

ረቡዕ፣ መጋቢት 7 2008
https://p.dw.com/p/1IEB4
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abukeker

ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የኢጣልያ ፕሬዝደንት ሴርጂዮ ማታሬላ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ድላማኒ ዙማ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ማታሬላና ዙማ ትኩረት ሰጥተው ከተነጋገሩባቸው መካከል የስደተኞች ጉዳይ ዋነኛው እንደነበር የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ማታሬላ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የስደተኞች ጉዳይ በአጭር ጊዜ መፍትሄ የሚገኝለት ችግር እንደማይሆን አስታውቀው ችግሩን ለማቃለል በርካታ ዜጎቻቸው የሚሰደዱባቸው ሃገራት ትብብር እንደሚያሻ ተናግረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ