የኢጣልያ ማሳሰቢያ
ሐሙስ፣ የካቲት 12 2007ማስታወቂያ
ኢጣልያ አውሮፓ ላይ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል ባለችው ራሱን የሶሪያና የኢራቅ እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው IS ላይ አፋጣኝ የተባበረ እርምጃ እዲወሰድ ጥሪ አቅርባለች ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት ለሃገራቸው ፓርላማ ባሰሙት ንግግር በሊቢያ ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት ሃገሪቱ የመሪነቱን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆንዋን አስታውቀዋል ።IS ኢጣልያ ውስጥ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል በሚል ስጋት ጥብቅ የፀጥታ ጥበቃ እንደሚካሄድ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማስታወቃቸውን የሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስ ዘግቧል ።
ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ