1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አልፈጥር አከባበር

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 4 2002

ኢድ ሙባራክ! ከአምስቱ የእስልምና አርካኖች መካከል የረመዳን ጾም ነገ አርብ እንደሚጠናቀቅ ተገልጾአል። ስለዚህም በአለም ዚርያ የሚገኙ የሃይማኖቱ ተከታዮች ኢድ አልፈጥርን በደማቅ ያከብራሉ።

https://p.dw.com/p/P7kW
ምስል AP

እንኳን ለኢድ አልፈጥር አደረሳችሁ፣ አድማጮች! በለቱ ዝግጅታችን የዘንድሮ ረመዳን ጾም እንዴት ነበር የአከባበሩስ ወግ እንዲት ነዉ ብለን በሳዉዲ አረብያ እንዲሁም እዚህ በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን አነጋግረናል ለቅንብሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ!
በአለም ዙርያ 1.3 ቢሊዮን የሚሆኑ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የረመዳንን ጾም አጠናቀዉ ነገ የረመዳን ኢድን ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸዉ ተዘግቦአል። እዚህ በጀርመን የሚኖሩ የቱርክ ተወላጆች ዛሪ ሃሙስ ኢድ አልፈጥርን በማክበር ላይ ናቸዉ። በጨረቃ የቀን መቁጠርያ ቀመር ዘጠነኛ ወር ላይ የሚደረገዉ ይህ የረመዳን ጾም በአብዛኛዉ የአለም አገራት ዛሪ ተጠናቆ የኢድ አልፈጥር በአል ነገ አርብ ሊከበር ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጽያዉያን ጾሙን እንዴት አሳለፉት በአሉንስ እንዴት ሊያከብሩ ተዘጋጅተዋል ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ